በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቱሪዝም ኮሚሽን የገልማ አባ ገዳ ማዕከል ለካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውሉ ከታች በተዘረዘረው መሰረት በንግድ ዘርፉ የተሰማሩ ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ መፈጸም ስለሚፈልግ ተፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ ድርጅቶችን /ግለሰቦችን/ ለ1ዓመት ውል በመግባት ግዥ መፈጸም መግዛት ስለሚፈልግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል /ጥሪ ያደርጋል/ ፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቱሪዝም ኮሚሽን የገልማ አባ ገዳ ማዕከል ለካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውሉ ከታች በተዘረዘረው መሰረት በንግድ ዘርፉ የተሰማሩ ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ መፈጸም ስለሚፈልግ ተፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ ድርጅቶችን /ግለሰቦችን/ ለ1ዓመት ውል በመግባት ግዥ መፈጸም መግዛት ስለሚፈልግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል /ጥሪ ያደርጋል/ ፡፡
የዕቃዎቹ ዝርዝር
ሎት 1፡- የምግብ ግብዓቶች፣ አትክልትና ፍራፍሬ
ሎት 2፡- ወተትና የወተት ተዋጽኦ ወዘተ
ሎት 3፡- ሌሎች የምግብ እህሎች የእንጀራ ሩዝ፣ ገብስ፣ የዳቦ/ስንዴ ዱቄት፣ እና ሌሎች የፋብሪካ ምርቶች
ሎት 4፡- የዶሮ ስጋ፣ የዓሳ ስጋ፣ እንቁላል፣
ሎት 5፡- የማገዶ እንጨት
ሎት 6፡- የቁም የእርድ ከብት (ለስጋ የሚሆን)
በዚሁ መሰረት:-
- ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የሚፈለግባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ አጠናቀ ስለመክፈላቸው በቂ ማስረጃ (ክሊራንስ) ማቅረብ የሚችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የንግድ መለያ ቁጥር (TIN) እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት (15) ተከታታይ ቀናት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቱሪዝም ኮሚሽን የገልማ አባ ገዳ ማዕከል ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 110 የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታ ሠነዱ ይህ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስራ አምስተኛው (15)ኛው ተከታታይ ቀናት ይሸጥና በአስራ ስድስተኛው (16)ኛው የስራ ቀን በ3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ከቀኑ 3፡30 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ለውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ላይ አስር ከመቶ (10/100) በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ አለበት፡፡
- የውል ማስከበሪያውም እሸናፊው ድርጅት ዕቃዎቹን በውሉ የጊዜ ገደብ እስገብቶ እስኪያጠናቅቅ ድረስ ተይዞ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን የምግብ ግብዓቶች ለማቅረብ ለ1 ዓመት ውል መፈረም ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች በራሳቸው የትራንስፖርት ወጪ ጭነው አዳማ ገልማ አባ ገዳ ማዕከል ጽ/ቤት ድረስ በማቅረብ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን በተናጠል በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ የድርጅቱ ማህተም አርፎበት መ/ቤቱ ለዚሁ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በጨረታው የመክፈቻ እለት ማስገባት አለባቸው።
- ሌሎች ዝርዝር ማብራሪያዎች ከሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቸላሉ፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ፡- 022 112 45 65/022 212 92 55 ደውለው አስፈላጊውን መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቱሪዝም ኮሚሽን የገልማ አባ ገዳ ማዕከል
