Tender Detail

Tender Details


በጨረታ ቁጥር ኢ.ሚ.ኔ.በ.ግ.ጨ 005/2018 ዓ.ም በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በጨረታ ቁጥር ኢ.ሚ.ኔ.በ.ግ.ጨ 005/2018 ዓ.ም በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ በመሆኑ በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ፦

ሎት 1 - የጀነሬተር፣ ዩፒኤስ እና እውቶማቲክ ትራንስፈር ስዊች ግዥ፤

ሎት 2 - የፕሪንተር ስካነር እና ፎቶ ኮፒ ማሽን በአንድ ላይ የሚሰራ ግዥ፤

ሎት 3 - የልብስ ማጠቢያ ማሽን ግዥ፥

ሎት 4 - የማይክ ሎጎ ግዥ በድጋሚ የወጣ

በጨረታ ቁጥር አሚ.አበግ.ጨ. 005/2018 ዓ.ም በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ በመሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ፡-

1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የገቢዎች ከሊራንስ ያላቸው፤

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉና በግዥ አቅራቢነት የተመዘገቡ፤

3. ተጫራቾች በሚያቀርቡት እያንዳንዱ ሰነድ እና በፓስታ ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማቸውን ማኖርይጠበቅባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ ለእያንዳንዱ ሎት 1. የጀነሬተር፣ ዩፒኤስ እና እውቶማቲከ ትራንስፈርስዊች ግዥ 500,000 ብር፣ ሎት 2 የፕሪንተር ስካነር እና ፎቶ ኮፒ ማሽን በእንድ ላይ የሚሰራ ግዥ 20,000 ብር፤ ሎት 3. የልብስ ማጠቢያ ማሽን ግዥ 50,000 ብር፤ ሎት 4. የማይከ ሎጎ ግዥ 20,000 ብር በባንክበተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የስራ ቀናት ውስጥ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርከ ቢሮ ቁጥር 6 ለሰነዱ ከፍያ 300 (ሶስት መቶ ብር) በመከፍል ዘወትር በሥራ ሰዓት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 28 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

6. ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች/ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ ሚዲያ ኔትወርከ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን ለመክፈት አያግደውም፡፡ የመከፈቻው ዕለት በዓል/ዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡

7. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ዋናውንና ኮፒውን/ ቴክኒካል ኦሪጅናል፣ ኮፒ እና ፋይናንሻል ኦሪጂናልና ኮፒ/ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

8. በአንዱ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡

9. በጨረታ ያሸነፈ ተጫራች ከመቤታችን ጋር ጨረታውን እንዳሸነፈ ካወቀበት ጊዜ አንስቶ በ15 ቀናት ውስጥ በሲፒኦ የጠቅላላ ዋጋውን 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይኖርበታል፡፡

10. ተቋሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ፡- የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርከ 5 ኪሎ ቅድስት ማሪያም ቤ/ክርስቲያን ከማህበረ ቅዱሳን ጀርባ ያለው ህንፃ፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011-1-11-63-82 መደወል ይችላሉ፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ

Save Tender