Tender Detail

Tender Details


የሸካ ማህበረሰብ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ኮምፒዩተር፣ ቪዲዮ ካሜራ እና ፎቶ ካሜራ አክሰሰሪዎች፣ FM Radio Transmission እና ሶላር ጄኔሬተር /solar battery and panel/ እና የቢሮ መኪና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የሸካ ማህበረሰብ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን ማለትም፡-

ሎት 01 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ኮምፒዩተር ቪዲዮ ካሜራ እና ፎቶ ካሜራ አክሰሰሪዎች፣

ሎት 02 FM Radio Transmission እና ሶላር ጄኔሬተር /solar battery and panel/

ሎት 03 የቢሮ መኪና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል።

  1. ከላይ የተጠቀሰውን ዕቃ ቀጥታ ግንኙነትና አግባብነት ያላቸውና የዘመኑን ወይም 2017 . የንግድ ፈቃድ ያሳደሱ፣ እንዲሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት እና የቫት /የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ሎት 01 ሎት 02 እና ሎት 03 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግሥት የሸካ ማህበረሰብ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት ገንዘቡን በመከፈል ደረሰኙን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን በቢሮያችን G+2 ሕንፃ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታውን የቴክኒካልና የፋይናንሻል ሰነድ በመለየት በታሸገ ፖስታ በማድረግ ኦሪጅናል እና ኮፒ በመለየት ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍ የሸካ ማህበረሰብ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ ሥራ ሂደት ቢሮ ለዚህ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  5. ይህ ማስታወቂያ በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15/ አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ይቆያል ፡፡
  6. ጨረታው 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከረፋዱ 430 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  7. 16ኛው ቀን የመንግሥት የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የመንግሥት የሥራ ቀናት ጨረታው በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ የሆነው አቅራቢ ዕቃዎችን አጓጉዞ በደቡብ ምዕራብ ///// ሸካ ዞን በማሻ ከተማ የሸካ ማህበረሰብ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት ማቅረብ አለበት፡፡
  9. ውል እንዲገባ ከተጻፈበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ዕቃዎችን በራሱ አጓጉዞ ማዘጋጀት /ማቅረብ/ አለበት፡፡
  10. ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ለማስያዝ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው፡፡
  11. የሚቀርቡ እቃዎች ጥራት ያላቸውና በተሰጣቸው እስፔስፊከሽን መሰረት አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፍል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ፡-047-558-0788 047-558-0965 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።

 

የሸካ ማህበረሰብ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት

Save Tender