Tender Detail

Tender Details


ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዴቨሎፕመንት ኢኒሼቲቭ (HUNDEE) በDutch Relief Alliance (DRA) የፋይናንስ ድጋፍና ከCordaid ጋር በመተባበር በሚተገብረው Ethiopian Joint Response (EJR) ፕሮጀክት ሥር በቦረና ዞን፣ በዱብሉቅ ወረዳ፣ ቦኮሳ ቀበሌ የውሃ ፓምፕ ማድረጊያ የሶላር ሲስተም አቅርቦት፣ መጓጓዝ፣ ተከላ፣ ሙከራ (Testing and Commissioning) እና ለአገልግሎት ዝግጁ አድርጎ የማስረከብ ሥራ በክፍት ጨረታ (Open National Competitive Bidding) ለማስፈጸም ስለሚፈልግ፣ በዚህ ዘርፍ ብቁና ተሞክሮ ያላቸውን ተጫራቾች ይጋብዛል።


የጨረታ ማስታወቂያ

ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዴቨሎፕመንት ኢኒሼቲቭ (HUNDEE)Dutch Relief Alliance (DRA) የፋይናንስ ድጋፍና ከCordaid ጋር በመተባበር በሚተገብረው Ethiopian Joint Response (EJR) ፕሮጀክት ሥር በቦረና ዞን፣ በዱብሉቅ ወረዳ፣ ቦኮሳ ቀበሌ የውሃ ፓምፕ ማድረጊያ የሶላር ሲስተም አቅርቦት፣ መጓጓዝ፣ ተከላ፣ ሙከራ (Testing and Commissioning) እና ለአገልግሎት ዝግጁ አድርጎ የማስረከብ ሥራ በክፍት ጨረታ (Open National Competitive Bidding) ለማስፈጸም ስለሚፈልግ፣ በዚህ ዘርፍ ብቁና ተሞክሮ ያላቸውን ተጫራቾች ይጋብዛል።

የተጫራቾች መስፈርቶች

  1. የ2026/2018 ዓ.ም. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ በዘርፉ የተመዘገበ ድርጅት መሆን አለበት።
  2. ትክክለኛ የግብር ከፋይ መለያ (TIN) እና አስፈላጊ በሆነ ሁኔታ የእሴት ታክስ (VAT) የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለበት።
  3. ሕጋዊ የፋይናንስ ደረሰኝ (VAT Receipt) መስጠት የሚችል መሆን አለበት።
  4. በጨረታ ሰነዱ የተገለጹትን ቴክኒካልና አስተዳደራዊ መስፈርቶች ማሟላት አለበት።

የጨረታ ሰነድ

  • የጨረታ ሰነዱን ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ከሁንዴ ዋና መሥሪያ ቤት መግዛት ይቻላል።
  • የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security/Bid Bond) ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 3%ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዴቨሎፕመንት ኢኒሼቲቭ ስም በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም Bank Guarantee ማቅረብ ያስፈልጋል።
  • የቴክኒክና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች በታሸገና በማኅተም በታተመ ኤንቨሎፕ በማስገባት መቅረብ አለባቸው።

የጨረታ ሰነድ መግዣና ማስገቢያ

የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 7 (ሰባት) የሥራ ቀናት  ውስጥ በአዲስ አበባ፣ መስቀል ፍላወር አደባባይ አካባቢ፣ ከቪላ ቨርዴ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የሁንዴ ዋና መሥሪያ ቤት በመቅረብ መግዛት ይቻላል።

የጨረታ ሰነዱን ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን የማስታወቂያው 7ኛ ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ ሲሆን፣ ጨረታው በዚያው ቀን በ4፡00 ሰዓት ይዘጋል።

የጨረታ መክፈቻ

ጨረታው በተዘጋበት ቀን ከጠዋቱ 430 ላይ በሁንዴ ዋና መሥሪያ ቤት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።

የአሸናፊው ግዴታ

አሸናፊው ድርጅት የሶላር ሲስተሙን ወደ ፕሮጀክቱ ቦታ በማጓጓዝ፣ በመትከል፣ የሙከራ ሥራዎችን (Testing and Commissioning) በማከናወን እና ለአገልግሎት ዝግጁ አድርጎ ለድርጅቱ ማስረከብ አለበት። የቴክኒክ ዝርዝር መግለጫ (Technical Specification) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ይሰጣል።

ልዩ ማሳሰቢያ

  • ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ያለምንም ምክንያት የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፦
ስልክ፡ +251913399817/ 011-558-2328

Save Tender