በጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የዕቅድ ማስፈፀሚያ የሚውሉ የአገልግሎት ግዥ የመኪና ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ግዥ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር
ጉ/ክ/ከ/ዋ/ስ/አስ/ፋ/ጽ/ቤት ግዥ ቡድን 03/2017 ዓ.ም
በጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የዕቅድ ማስፈፀሚያ የሚውሉ የአገልግሎት ግዥ የመኪና ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1. የመኪና ጥገና (ሰርቪስ)
ስለዚህ በዚህ የሥራ ዘርፍ ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
- በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፣
- የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1. 40,000 ብር
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር እያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ዝርዝር ጉዳዮችና የተጫራቾችን መመሪያ የያዘ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 150.00 /አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ በመግዛት 9ኛ ፎቅ መውሰድ ይችላሉ፤
- ጨረታው መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀን ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 4 ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው የሚታሸግበት ቀን በ10ኛ ቀን 11፡30 ይሆናል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የሚከፈትበት ቦታ 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል ህጋዊ ወኪል ለመሆናቸሁ የሚገልጽ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ እያንዳንዱ ሰነድ ላይ ማህተም ማድረግ አለበት፡፡ /VAT/ ያካተተ መሆኑን ወይም አለመሆኑን መጥቀስ ይኖርበታል ካልተጠቀሰ እንደተካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
- ኦርጅናል እና ኮፒውን ሰነድ ለየብቻ አድርጎ በማያያዝ ማስገባት ይኖርበታል፣
- በጨረታው ላይ የእቃውን ብዛት 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይቻላል።
- በውሉ ላይ 25% መጨመር ይቻላል።
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በበጀት ዓመቱ ሙሉውን ዓመት የዋጋ ማስተካከያ የማናደርግ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-
አድራሻ፡- አዲሱ ገበያ ኖክ ጀርባ የጉ/ክ/ከተማ አዲሱ ህንጻ 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 04
በስልክ ቁጥር ፡- 0921770036 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት
