በሲዳማ ብ/ከ/መ/የትምህርት ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የመምህራን ማሰልጠኛ ተሽከርካሪ ጥገና ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ማስጠገን ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/ 2019
በሲዳማ ብ/ከ/መ/የትምህርት ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የመምህራን ማሰልጠኛ ተሽከርካሪ ጥገና ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ማስጠገን ይፈልጋል።
ከዚህ በላይ በተዘረዘሩት በውድድር ለመሳተፍ የሚፈልጉ፡-
- በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው እንዲሁም 3ኛ ደረጃ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ዋጋቸውን የሚገልፀውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ ከግ/ፋ/ን/አስ/ርዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት አለባቸው፤
- የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 21ኛው ቀን ከጥዋቱ 3፡00 – 6፡00 ድረስ ብቻ ለዚህ አላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ከክልሉ የትራንስፖርት ደረጃ ሶስት የሚገልጽ ብቃት ማርጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ከላይ የተገለጹ የተሽከርካሪ ጥገና የጠቅላላ ሽያጭ ከብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢዎች ብቻ መጫረት የሚችሉ መሆኑን፣
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ 90 ቀን ጸንቶ የሚቆይ ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ብቻ በሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ / ማቅረብ አለባቸው፤
- ጨረታው ለ3 ወራት /90 ቀናት/ ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች በቴክኒካል ሰነድ ተጫራቾች መመሪያና ጠቅላላ የውል ሁኔታዎች መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፤
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስ/ርዳይሬክቶሬት ግዥ ከፍል ቁጥር 14 ማግኘት ይቻላል።
- በጨረታ ግምገማ ወቅት በሀዋሳ ከተማ ላይ ባሉት ጋራዥ የመስክ ምልከታ የሚደርግ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሣሰቢያ፡- ሽያጩ ቫትን ጨምሮ ከብር 20,000.00 /ሀያ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ከቫት ተመዝጋቢዎች ላይ ቫቱን ቀንሰን የምናስቀር መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 046-212-43-07
የሲዳማ ብ/ክ/መ/ት ትምህርት ቢሮ ሀዋሳ
✨ messages.ai_summary
Open tender for repair of teacher training vehicles by the Sidama Regional Education Bureau, Hawassa. Bidders must hold a valid trade license, current tax clearance, and a third-level transport competency certificate. Field inspection of garages in Hawassa will be conducted.
