አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 98/90 መሠረት የተረከባቸውን መኖሪያ ቤቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 01/2018
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 98/90 መሠረት የተረከባቸውን መኖሪያ ቤቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
- በግልጽ ጨረታ የሚሸጠው ንብረት ዝርዝር፤
| ተ.ቁ | የንብረቱ አይነት | አድራሻ | የባለቤትነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት | የጨረታ መነሻ ዋጋ | ጨረታ የሚካሔድበት ቦታ (ቅርንጫፍ) | ||||||
| ከተማ | ወረዳ | ቀበሌ | የቦታው ስፋት | ቦታ | ቀን | የጨረታ መዝጊያ ሰዓት | ጨረታ መክፈቻ ሰዓት | ||||
| 1 | መኖሪያ ቤት | አክሱም | - | 5 | 250 | 391/መ/2002 | 5,614,904,33 | በባንኩ ዋና መ/ቤት እና አክሱም ቅርንጫፍ | |||
| 2 | መኖሪያ ቤት | አክሱም | - | 5 | 250 | 392/መ/2007 | 5,614,904.33 | 17/02/2018 ዓ.ም | ከጠዋቱ 3፡30 | ከጠዋቱ 4፡00 | |
| 3 | መኖሪያ ቤት | ሽረ እንደስላሴ | - | 3 | 250 | 1744/4085/11 | 7,829,234.34 | በባንኩ ዋና መ/ቤት እና ሽረ እንዳስላሴ ቅርንጫፍ | |||
በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
- የጨረታ መክፈቻና መዝጊያ ከላይ በሰንጠረዥ በተገለፀው ቦታ፤ ቀን እና ሰዓት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ወይም ኮሚቴዎች በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል። ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በኋላ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
- ተጫራቾች የንብረቱን የጨረታ ሰነድ ሃያ ሁለት የቀድሞ ዘሪሁን ህንፃ ፊት ለፊት በባንካችን ዋናው መ/ቤት ሌክስ ፕላዛ ህንፃ 4ኛ ወለል ከጥቅምት 03 ቀን 2018 ዓ.ም ግዢና ፋሲሊቲስ ማኔጅመንት መምሪያ እና በባንኩ አክሱም እና ሽረ እንደስሳሴ ቅርንጫፍ በአካል በመቅረብ 115.00 ብር በመክፈል ሰነዳን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የንግድ ቤቱን የሚገዙበትን ዋጋ በመጥቀስ ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በማያያዝ በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዝርዝሩ ከላይ በቀረበው የንብረቱ መጫረቻ ቦታ፣ ቀን እና ሰዓት ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን የመወዳደሪያ ሰነዳችሁን ማስገባት ይኖርባችኋል። በመወዳደሪያ ሰነዳችሁ ላይ የተጫራች ስም፣ ፊርማ እና ስልክ ቁጥር መፃፍ አለበት።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በአሃዝ እና በፊደል እንዲሁም ከቫት በፊት እና በኋላ መሆኑ መግለፅ አለባቸው። የሚያቀርቡት ዋጋ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጎኑ በተጫራች መፈረም አለበት።
- ተጫራች የመጫረቻ ዋጋ በቀላሉ በሚጠፋ ወይም በእርሳስ መሙላት የለበትም።
- የጨረታው አሸናፊ ከንብረቱ የሚፈለገውን ማንኛውንም ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ክፍያ ማለትም የስም ማዘዋወሪያ ክፍያዎችን፣ ሌሎች የግብር ክፍያዎችን እና ለድርጅት ቤቱ በቀረ የሊዝ ዘመን የሚከፍለውን የሊዝ ክፍያ ዕዳ አንዲሁም ተዛማጅ ወጪዎች ተ.እ.ታን ጨምሮ መሉ በመሉ የሚከፍል ይሆናል::
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ተጫረች ለጨረታ ማስከበሪያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4) ወይም 25% በባንክ በተረጋገጠ በክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ /CPO/ በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ስም አሰርተው በታሸገ ኢንቬሎፕ ከነሙሉ አድራሻው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፈበትን ሙሉ ክፍያ በመፈፀም ያስያዘውን ሲፒኦ (CPO) መውሰድ የሚችል ሲሆን ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 7 የስራ ቀናት ጊዜ ውስጥ ይመለስላቸዋል።
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ዋጋ ከነ ተጨማሪ እሴት ታክለ (15%) ጨምሮ መክፈል ይኖርበቃል። ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻለ የጨረታው አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው ሲፒኦ (CPO) ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
- ተጫራቾች ስለእያንዳንዱ ንብረት ዝርዝር እና ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን በተመለከተ ሃያ ሁለት የቀደሞ ዘሪሁን ህንፃ ፊት ለፊት በባንካችን ዋናው መ/ቤት ሌክስ ፕላዛ ህንፃ 4ኛ መለል ግዢና ፋሲሊቲስ ማኔጅመንት መምሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-6-36-20-64 እንዲሁም ሰሜን ሪጅን ፅ/ቤት 034-771-37-00 ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የድርጅት ቤቱን ለመጎብኘት የባንኩ አክሱም እና ሽረ እንደስላሴ ቅርንጫፍ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 034-771-37-00 በመደወል ስማቸውን በማስመዝገብ ባንኩ በሚያወጣው መርሐ ግብር መሰረት መመልከት ይችላሉ።
- ባንኩ ንግድ ቤቱ አሻሻጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ሽያጩን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
