በድሬዳዋ አስተዳደር የድል ጮራ ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች UPS በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለፈለገ ህጋዊና ብቁ ተወዳዳሪዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ድ/ዳ/ድ/ጮ/ሆ/04/18
በድሬዳዋ አስተዳደር የድል ጮራ ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች UPS በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለፈለገ ህጋዊና ብቁ ተወዳዳሪዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት በጨረታው ላይ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች
- ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የ2018 ዓ/ም ግብር የከፈሉ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- በመንግስት ግዢ አቅራቢ የተመዘገቡና የተመዘገቡበትን ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የታክስ መለያ ቁጥር (TIN No) ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለዕያንዳንዱ ሎት በመክፈል በድል ጮራ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 155 በመቅረብ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።
- መስፈርቱን የሚያሟላ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም (CPO) ከጨረታው ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ መቀበያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነዱ የሚከፈትበት ቀን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4:00 ሠዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙብት በሆስፒታሉ ግዢ ፋ/ን/አስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 155 ይከፈታል።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ እንደተገለፀለት አስፈላጊውን የጨረታ ውል ማሰከበሪያ በማስያዝ ከሆስፒታሉ ጋር ውል መፈራረም አለበት። ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን እና ፈርማቸውን እንዲሁም የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሎም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:- በድሬዳዋ አስተዳደር የድል ጮራ ሆስፒታል
ስልክ ቁጥር፡- 0982540408/0901103211/2-521115693 ፖስታ 177
በድሬዳዋ አስተዳደር የድል ጮራ ሆስፒታል
