የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በ19/02/2018 እና በ22/02/2018 ዓ/ም በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በ19/02/2018 እና በ22/02/2018 ዓ/ም በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባለበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በሟሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣሎት የምትፈልጉት የእቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እንዲመጣሎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የጨረታ መስፈርቶች፡-
- ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክሰ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለ መሆኑ ክሊራንስ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅሰቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫረቶች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን በ19/02/2018 እና በ22/02/2018 ዓ/ም እስከ ጠዋቱ 3፡45 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ።
- ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና (cpo) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ አንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሰም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጨራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (እሰኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ፡፡
|
የጨረታ ቦታ |
የጨረታው ዓይነት |
ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች |
የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት |
ግልጽ ጨረታ እና በሐራጅ |
ጫማዎች፣ አልባሳት፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ምግብ ነክ የስፖርት እቃዎች፣ የእጅ ሰዓት ኮስሞቲክስ፣ መነፅር እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች
|
ለግልጽና ለሐራጅ ጨረታ በ19/02/2018 እና 022/02/2018 እስከ ጠዋቱ 3፡45 |
ለግልጽ ጨረታ በ19/02/2018 እና በ22/02/2018 ከጠዋቱ 4፡00 ሲሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ በ19/02/2018 እና በ22/02/2018 ዓ/ም 5፡00 ሰዓት ይሆናል። |
- የጨረታው መክፈቻ ቦታ:- በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡
- ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (C.P.O) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውሰጥ ተመላሸ ይደረግላቸዋል፡፡
- ከአሸፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውሰጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖረበታል፡፡
- ከላይ በተ.ቁ.7 በተገለጹት ቀናት ውሰጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረከበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው የጨረታ ማስከበሪያ ያሰያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሸኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሜ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
- ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በጉምሩክ ኮሚሽን የአዋሽ ቅ/ጽ/ቤት
