የሲዳማ ብ/ክ/መ/ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሎት የተገለጸውን ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብ/ክ/መ/ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሎት የተገለጸውን ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ ግዥ
- ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያ ግዥ
- ሎት 3. የመኪና ጥገና ግዥ
- ሎት 4 መጋረጃና የወለል ምንጣፍ ግዥ
በመሆኑም ተጫራቾች፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) በላይ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) እየከፈሉ ከመ/ቤቱ ግዥ ፋይናስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት መውሰድ ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር ብቻ) በጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ጨረታው የቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ እና የፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ መቅረብ አለበት። ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 11ኛው ቀን 8:00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ በ8፡00 ሰአት ተዘግቶ በ8፡30 የሚከፈት ይሆናል፣
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ስማቸውንና፣ ፊርማቸውን፣ አድራሻቸውንና ስልክ ቁጥር ማስፈር አለባቸው፣
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0462217014 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የመ/ቤቱ አድራሻ ከሀዋሳ የሲዳማ/ብ/ክ/መ/ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ጎን ነው፡፡
የሲዳማ/ብ/ክ/መ/ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ
