የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለዋናው መ/ቤት ሰራተኞች የዓይን መነፅር ሥራ አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር RE-LP/OT/10/SIG/2018
- የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለዋናው መ/ቤት ሰራተኞች የዓይን መነፅር ሥራ አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ ለ2017/18 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታክስ ክሊራንስ በጨረታ መሳተፍ እንዲችል የድጋፍ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No) ሠርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ የሚመለከተው የመንግስት አካል ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች አገልግሎት ሰጪ ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ሂሳብ ቁጥር 1000000888862 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታውቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ፣ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-11፡00 ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
ግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ
ሜክሲኮ አካባቢ ከሚገኘው አልሳም ጨለለቅ ህንፃ ፊት ለፊት፣ ፈሊፒስ ህንፃ
2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220
ስልክ ቁጥር +251 11 5 50 04 17 ወይም 011 5 51 62 71
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 3 በተገለፀው አድራሻ ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) በባንክ የተመሠከረለት የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከቴክኒክ መጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለዘጠና (90) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
- የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለስልሳ (60) ቀናት ይሆናል።
- ግሩፑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
