ቦሌ ማተሚያ ኃላ/የተ/የግል ማህበር የተለያዩ አሮጌ ማሽነሪዎች ባሉበት ሁኔታ ወይም በብረት መልክ በኪሎ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የሀገር ውስጥ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ቦሌ ማተሚያ ኃላ/የተ/የግል ማህበር የተለያዩ አሮጌ ማሽነሪዎች ባሉበት ሁኔታ ወይም በብረት መልክ በኪሎ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት፤ የንግድ ሰርተፊኬት እና ሌሎችም የህጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በቅድሚያ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ ቢሮ ቁጥር 101 በመክፈል ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ድረስ ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ በሚገኘው ቢሯችን መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ቴከኒካል እና ፋይናንሽል ሰነዶችን በአንድ ፖስታ አሽገው የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከግዥ ክፍል በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ያስገባሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በቀረበው ቅጽ መሰረት ባለበት ሁኔታ ወይም በኪሎ ብሎ በመጻፍ እና ተእታ 15% በማካተት በግልጽ ጽፈው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በኪሎ ሃሳብ ተወዳድረው ያሸነፉ ተጫራቾች ከኖሩ ማህበራችን ለዚህ የሚመጥን ሚዛን ስለሌለው ከውጭ በጋራ በመውሰድ በሚመለከተው ህጋዊ ስፍራ የሚመዘን ሆኖ የሚዛን ወጪው በተጫራቹ ይሸፈናል፡፡
- ተጫራቾች ዘወትር በስራ ሰዓት በማህበሩ ግቢ በመምጣት እቃዎቹን ማየት ይችላሉ፡፡
- በአይነትም ይሁን በኪሎ ተወዳድሮ ያሸነፈው ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለጸለት ቢዘገይ በ8 ቀናት ውስጥ ያሸነፈውን እቃ ሙሉ ዋጋ በመክፈል እቃውን አጠቃሎ የማንሳት ግዴታ ያለበት ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካላነሳ ያስያዘው ሲፒኦ ተወርሶ ለሚቀጥለው ተጫራች እድሉ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 15ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማህበሩ የስብሰባ አዳራሽ/ የግዢ ክፍል ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን በዝግ ቀን ከዋለ በቀጣይ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ ሌላ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ- ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ
ስልክ ቁጥር:- 011-1-51-5-50-05/ 011-5-51-88-72
ፋክስ ቁጥር፡- 011-5-51-86-96
ፖ.ሳ.ቁጥር:- 2365
ቦሌ ማተሚያ ኃላ/የተ/የግል ማህበር
