Tender Detail

Tender Details

  • Company በጋሞ ዞን የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት
  • Address በጋሞ ዞን አርባምንጭ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-181-40-91
  • Website
  • Deadline21 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2025-11-21 00:00:00
  • Categories Electronics Materials , Vehicle Spare Parts

በጋሞ ዞን የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው የመጀመሪያ ዙር ያልተሳኩ የተለያዩ ዕቃዎች ግዥ ማለትም ሎት-1 የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች፣ ሎት-2 የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎች፣ ሎት-3 የተለያዩ አዲስ ሞቴር ሳይክል ባለሁለት እግር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

በጋሞ ዞን የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው የመጀመሪያ ዙር ያልተሳኩ የተለያዩ ዕቃዎች ግዥ ማለትም ሎት-1 የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች፣ ሎት-2 የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎች፣ ሎት-3 የተለያዩ አዲስ ሞቴር ሳይክል ባለሁለት እግር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት በዘርፉ የተሰማሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች በጨረታው መወዳደር የሚችሉት ለጨረታው ውድድር ማቅረብ ያለባቸው መሰፈርት የታደሴ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብርመከፈያ መለያ ቁጥር ሰርትፍኬት፣ የአቅራቢነት ሰርትፍኬት፣ የንግድ ምዝገባ ሰርትፍኬት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አባሪ አድርገው ማቅረብ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከመ/ቤቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር በመቅረብ ዘውትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ በ200 በመከፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በቢድ ቦንድ በግዥ መመሪያ ላይ ከተፈቀዱ ዘዴዎች በአንደኛው በባንክየተረጋገጠ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡

የዕቃ የጥራት ጉድለት በሚታይበት ጊዜ አቅራቢው ወዲያውኑ የማስተካከልና የመቀየርኃላፊነት አለበት፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ዋጋውን ሲሞሉ ሰነዱን ያለሥርዝ ድልዝ በመሙላት በሁሉም ገጽ ላይበመፈረምና የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍ በፖስታ ታሽጎ በፖስታው ላይም የጨረታው ዓይነት ስልክና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ በዕለቱ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

ጨረታውን ያሸነፈ አካል ከመ/ቤቱ ጋር ውል በመግባት ጥራቱንና ወቅታዊነቱ የጠበቀው ዕቃ እስከ መ/ቤታችን ድረስ የትራንስፖርትና የአውራጅ ወጭውን ችሎ በማምጣት ለማስረከብ ፈቃደኛ የሆነ መሆን አለበት፡፡

ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት በአየር ላይቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዕለቱ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በመ/ቤቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር ከፍል ይከፈታል፡፡16ኛው ቀን የሥራ ቀን ሳይሆን ቢቀር በሚቀጥለው የሥራ ቀን ሂደቱ በተመሳሳይ ሰዓት ይከናወናል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፍል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 ማሳሰቢያ፡- በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ፊርማና ማህተም ማድረገዎን ያረጋግጡ፡፡

ስልክ:-046-1-81-40-91

የጋሞ ዞን የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender