የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ የተለያዩ የተሰባበሩ የአልጋ ብረታ ብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ የተለያዩ የተሰባበሩ የአልጋ ብረታ ብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ የጨረታውን ሰነድ በመግዛት ጨረታው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ጨረታውን ለመወዳደር የምትፈልጉ፡-
- የጨረታው ሰነድ የተዘጋጀው በኦሮምኛ ቋንቋ ስለሆነ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት /ከሰኞ እስከ ዓርብ/ ባለው ጊዜ ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ ፋይናንስ ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጠቅላላ ዋጋ ለውድድር ያቀረቡትን 10% የጨረታ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ አሽጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚሸጡ ብረታ ብረቶችን አስመልክቶ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡30 በአካል በመቅረብ ማየት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በተናጥል በፖስታ አስገብተው ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታው ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ቆይተው በ11ኛው ቀን ጠዋት እስከ 4፡00 ሰዓት ተሸጦ የጨረታው ሰነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ በዚሁ ዕለት ጠዋት 4፡30 ታሽጎ በ4፡45 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ በኮሌጁ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አጠቃላይ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር:- 0911909586/0913015046 ደውለው ይጠይቁ።
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ
