በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ ለትምህርት ከዚህ በታች በዩኒሴፍ ገንዘብ ድጋፍ በአራት ሎት የቀረቡትን እቃዎች ግዥ ለመከናወን ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ዘዴ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 08/2018
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ ለትምህርት ከዚህ በታች በዩኒሴፍ ገንዘብ ድጋፍ በአራት ሎት የቀረቡትን እቃዎች ግዥ ለመከናወን ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ዘዴ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
- ሎት 1. የድምጽ መሳሪያ ግዥ
- ሎት 2. የህጻናት ፕላስቲክ ወንበርና ጠረጴዛ ግዥ
- ሎት 3. የሴት ተማሪዎች ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ግዥ
- ሎት 4. የጅባ ግዥ
ከዚህ በላይ ለተዘረዘሩት በውድድር መስፈረት መሰረት ለመሣተፍ የሚፈልጉ፡-
- በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን አለባቸው፣ የተጫራቾች የአቅሪቢነት ምዝገባ የተመዘገቡ
- ተጫራቾች ዋጋቸውን የሚገልፀውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ ከግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ከግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 14 በአካል በመቅረብ መግዛት አለባቸው።
- የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 21ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:00 - 6:00 ሰዓት ድረስ ብቻ ለዚህ አላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ21ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ይከፈታል፤ ሆኖም 21ኛው ቀን የስራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ90 ቀን ጸንቶ የሚቆይ ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ/ በሲፒኦ ወይም አንኮንዲሽናል ባንክ ጋራንቲ በማቅረብ መወዳደር አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታውን በሚወዳደሩ በፖስታ በማሸግ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንት ለየብቻ በማድረግ ከሁለት ኮፒ ጋር ማቅረብ አለባቸው። በሎት 2 እና 3 የእቃው ናሙና የጨረታ ሰነድ በሚገባበት ወቅት መቅረብ አለበት፡፡ ሳምፕል ያላቀረበ ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይሆናል፡፡
- ጨረታው ለ3 ወራት /90 ቀናት ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ማግኘት ይቻላል። አንድ ተጫራች ከአንድ ሎት በላይ መወዳደር አይችልም፡፡
- ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሣሰቢያ፡- ሽያጩ ቫትን ጨምሮ ከብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር በላይ ለሆነው ግዥ 50% ቫት ቀንሰን የምናስቀር መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 046-221-7002/3 ደውለው ይጠይቁ።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ (ሀዋሳ)
