በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ስር የሚገኘው የራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል ለ2018 ዓ.ም ለጂም አገልግሎት የሚውሉ ማሽኖች መለዋወጫ ግብዓቶች እና የስፖርት ትጥቆች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ለጂም አገልግሎት የሚውሉ የማሽን መለዋወጫ ግብዓት ጨረታ 17/02/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ስር የሚገኘው የራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል ለ2018 ዓ.ም ለጂም አገልግሎት የሚውሉ ማሽኖች መለዋወጫ ግብዓቶች እና የስፖርት ትጥቆች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነድ ጋር ማንነታቸውን የሚገልጽ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ መታወቂያ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሕጋዊ በሚወዳደርበት ዘርፍ የንግድ ፈቃድ (የአቅራቢ ምዝገባ ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት ተመዝጋቢ፤ የቫት ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቧቸው የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ሙሉ ስም፣ አድራሻ፣ ክፍለ ከተማ፣ የቤት ቁጥርና የስልክ ቁጥራቸው መገለጽ አለበት፡፡
- በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ወይም የሕጋዊ ወኪሉ ስም እና ፊርማ ማህተም ያረፈበት መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የጨረታ ሰነድ በራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል 1ኛ ፎቅ ላይ ፋ/ግ/ን/አስ/ ቢሮ ቁጥር 2 ቀርበው የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ከፍለው ሰነዱን መግዛት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ በመሙላት ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አድርጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መጨመር ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቶች ማእከሉ ባወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ የግብዓቶች ዋጋ በማስፈር የማቅረብ እና የድርጅቱ ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል ስም የተሠራ ሲ.ፒ.ኦ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ከጨረታ ፖስታ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት በ10ኛው የሥራ ቀን 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል 1ኛ ፎቅ ላይ በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ከገዙት ጨረታ ሰነድ ውጪ ተሞልተው ለሚመጡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- ከተባለው ቀንና ሰአት በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ማእከሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በመሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዕቃ ናሙና ማስታወቂያ ከወጣበት 10ኛው (ጨረታ በሚከፈትበት) ቀን 4፡30 እስከ 5፡30 ባለው ሰዓት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተባለው ሰአት ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከውድድሩ ይሰረዛል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ተወዳድረው ካሸነፉ በኋላ ያሸንፉበትን ግብአት በተሰጠው የጊዜ ገደብ ለማቅረብ ፈቃደኛ ካልሆኑ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል ለሚመለከተው አካልም በደብዳቤ ይገልፃል።
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ የትራንስፖርት አገልግሎት ማእከሉ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አጠገብ ወይንም መድኃኒያለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤ ትልቁ አደባባይ ግሩም ሆስፒታል በሚወስደው 100 ሜትር በስተግራ ገባ ብሎ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማእከል
አዲስ አበባ
