የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ግዢ በድጋሚ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሀ. ሎት-1 የምግብ ቁሳቁስ (ዳይጄስቲቭ ብስኩት እና የህፃናት ወተት)
- ለ. ሎት-2 ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች (የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ሞዴስ /Sanitary Pad/
በመሆኑም በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በዘርፉ የተሰማሩ የዘመኑ የመንግስት ግብር የከፈሉ ወይም የ2017 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያደሱ ፣ በጨረታው መሳተፍ የሚያስችል ከገቢዎች ክሊራንስ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ እና የግብር መለያ ስርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አንዱ ተጫራች በሌላዉ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት ከጨረታዉ የሚያሳግድ ይሆናል።
- ተጫራቾች ከጨረታው በኋላ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ለሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ (2%) በCPO ወይም ባንክ ጋራንቲ አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር መሆኑን ወይም አለመሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራች ጨረታውን በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስራ አምስት (15) የስራ ቀናት ውስጥ ጨረታ ሰነዱን በጉርድ ሾላ ሳሊህተ ምህረት ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ድራር ሞል አጠገብ ከሚገኘዉ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመገኘት የጨረታዉን ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ በብር (800) ብር (ስምንት መቶ ብር) በመግዛት የጨረታ ሰነዳችሁን እስከ ሰኞ ህዳር 8/ 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራች ጨረታውን አሸንፎ ባቀረበዉ ሰነድ መሰረት እቃዎቹን ሳያቀርብ ቢቀር ያስያዘዉ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ድርጅቱ ገቢ ያደርጋል ወይም ተመላሽ አይሆንም።
- ጨረታ ሰነዶችና ከጨረታዉ ጋር ተያያዥ የሆኑ ሰነዶች ማለትም ቴክኒካል ዋናውና ኮፒ እና ፋይናንሻል ዋናውና ኮፒ ዶክመንት በፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያዉ ሰዓት በፊት ለዚህ በተዘጋጃዉ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ቁሳቁሶች የአገልግሎት ጊዜያቸው አንድ አመትና ከዚያ በላይ መሆን ያለበት ሲሆን ለዚህም ለሚያቀርቧቸው ቁሳቁሶች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ሳይቀይሩ በትእዛዙ መጠን እስከ 25 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው።
- ጨረታው ሰኞ ህዳር 8/2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 8፡30 በጉርድ ሾላ በሚገኘዉ ሳሊህተ ምህረት ቤተክርስያን ፊት ፊት ለፊት ድራር ሞል አጠገብ በሚገኘዉ የማህበሩ መሰብሰቢያ አደራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል።
- አሸናፊው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተገለፀለት ወይም የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ምግብ ነክ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ከ7ቀን ባልበለጠ ጊዜ ወይም በውሉ መሰረት ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ምግብ ነክ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን በድርጅቱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጫራቾች ስለጨረታዉ ተጨማሪ ማብራሪያ ሲፈልጉ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ስልክ በመደወል ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር
አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር : 011-515-06-08
ፖስታ ሳጥን ቁጥር፡ 41076
