የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ሚ/አ/ከ/ዋና ማዘጋጃ ቤት በባለቤትነት ለሚያሰራው ለመንገድ ጥገና ስራ አገ/ት የሚውል የዶዘር ማሽን ኪራይ በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ሚ/አ/ከ/ዋና ማዘጋጃ ቤት በባለቤትነት ለሚያሰራው ለመንገድ ጥገና ስራ አገ/ት የሚውል የዶዘር ማሽን ኪራይ በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላል፡፡
- ተጫራቾች በማሽነሪ ኪራይ የሥራ መስክ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው
- በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- ግብር ስለመክፈላቸው ከገቢዎች መ/ቤት ክሊራንስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ከግዥ ኬዝ ቲም የሥራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን ብር /500/ አምስት መቶ ብር ከፍለው በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ሞልተው ሲመልሱ ቴክኒካሉን 1 ኦርጅናልና 2 ኮፒ ፋይናንሻሉን 1 ኦርጅናልና 2 ኮፒ በሁለት ፖስታ በማድረግ እና በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ 400,000 /አራት መቶ ሺህ ብር/ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ ቼክ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና በባንክ የተረጋገጠ ለተርኦፍ ክሬዲት ለሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በማለት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን 4፡00 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
- ሰነዱን ሞልተው ወደ ጨረታ ሳጥን ለማስገባት ሲመጡ ተመዝግበውና ፈርመው ማስገባት አለባቸው፡፡
- በጨረታው ማስታወቂያ ላይ የትርጉም ስህተት ቢኖር በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፀው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
