የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሚ/አ/ከ/አስ/ር ኢንዱስትሪና ንግድ ጽ/ቤት ለሰንበት ገበያ አገ/ት የሚውል ድንኳን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሚ/አ/ከ/አስ/ር ኢንዱስትሪና ንግድ ጽ/ቤት ለሰንበት ገበያ አገ/ት የሚውል ድንኳን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላል፡፡
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው
- የጨረታ ሰነድ ከግዥ ክፍ/ንብ/አስ/ር ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን /በነጻ/ በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱ ሞልተው ሲመልሱ ሕጋዊነት ሰነድ እና ፋይናንሻል የተሞላበትን ሰነድ 1 ኦርጅናልና 1 ኮፒ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ሰነዱን ሞልተው ወደ ጨረታ ሳጥን ለማስገባት ሲመጡ ተመዝግበውና ፈርመው ማስገባት አለባቸው
- በጨረታ ማስታወቂያ ላይ የቃላት ወይም የትርጉም ስህተት ቢኖር በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጠው የበለጠ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ /ኢ/ል/ጽ/ቤት
