የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በ2018 በጀት አመት በı ሎት የተለያዩ ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ/አ/ከ/አ/ሴ/ህ/ማ/ጉ/ ቢሮ (04/001-001/2018)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በ2018 በጀት አመት በı ሎት የተለያዩ ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ሎት ቁጥር |
የሚገዛው እቃ/አገልግሎት |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን |
|
ሎት1 |
የተለያዩ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የቤት ውስጥ መገልገያ እቃዎች ግዥ |
100,000.00 CPO |
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግዥና የፋይናንስ መመሪያዎች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መኖራቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ተጨማሪ እሴት ታክስ /NAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ለአንድ ሎት 100 /መቶ ብር/በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአካውንት ቁጥር 1000009650559 በመከፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት እስከ 11 ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ከቢሮው ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በስፔስፊኬሽኑ መሰረት ብቻ ሞልተው እና አሽገው በአንድ ኤንቨሎፕ ላይ ኦርጂናልና ኮፒ ብለው በመለየት የግዥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
7. ተጫራቾች ሌሎች መረጃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
8. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ጨረታው በሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
9. ተጫራቾች ናሙና ለተጠየቀባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው
10. የጨረታ ማስከበሪያ በCPO ነው
ማሳሰቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይታሽጎ 4፡30 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
አድራሻ - አ/አ/ሴ /ህ/ማ/ጉ) ቢሮ ደጃች ውቤ ከጊዮርጊስ ቤተክሪስቲያን ወደ አፍንጮ በርበሚወስደው መንገድ የስድስት ኪሎ/ፈረንሳይ ታክሲ መጫኛ ጋር ህንጻ 1888 ላይ 2ኛ ፎቅ ስ.ቁጥር 0942129492/0947951760
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
