Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Agriculture Bureau (የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ)
  • Address ባሕር ዳር : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: +251583207115
  • Website
  • Deadline08 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • opening date2025-12-08 00:00:00
  • Categories Plastic Raw Materials And Products , Others

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የግብርና ቢሮ በተፈጥሮ ኃብት መሬት አጠቃቀም ዳይሬክቶሬት አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ ባለ 10, ሎት- 2 የእጅ ጋሪ እና የዉህ ማጠጫ ጀርዲን ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅቶች ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 04

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የግብርና ቢሮ በተፈጥሮ ኃብት መሬት አጠቃቀም ዳይሬክቶሬት አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ ባለ 10, ሎት- 2 የእጅ ጋሪ እና የዉህ ማጠጫ ጀርዲን ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅቶች ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶችና ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

1. በዘርፉ የተሰማሩ እና በዘመኑ ስለመታደሱ የሚገልጽ እና ግብር የከፈሉበትን ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. የግብረ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው

3 የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ የሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

4 ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማደረግ ከኦርጅናሉ ጋር በማገናዘብ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር እያይዘው ማቅረብ አለባቸው::

5. የሚገዙ የችግኝ ማፍያ ፕላስቲከ ጆርዲን እና የዕጅ ጋሪ ግዥ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ እና መቅረብ ያለባቸው አስፈላጊ መረጃወች በጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።

6 ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000.00/አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 14 ማግኛት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ብር ጠቅላላ የዕቃ የግንባታ ወይም የአገልግሎት ዋጋ ብር በቁርጥ ለሎት 1 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር እንዲሁም ለሎት 2- 100,000.00/አንድ መቶ ሺህ ብር ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (C.P.O) እና በቅድመ ሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ( Uncon-ditorial Bank Guarantee) ብቻ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው ማንኛወም ተጫራች የጨረታ /የመወዳደሪያ ሃሳቡን የቴከኒካል ሰነድ ዋና እና ቅጅ ለየብቻው እና የፋይናሽያል ሰነዱን እና የጨረታ ማስከበሪያውን በአንድ ዋና እና ቅጅ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በከልሉ ግብርና ቢሮ ግቢ ውስጥ ቢሮ ቁጥር 025 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም ለተጠቀሱት ግዥዎች ናሙናቸውን ከቴክኒካል ሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው።

8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በክልሉ ግብርና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 16 ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 400 ታሽጎ 430 ይከፈታል።

9 /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠ ነው።

10 በጨረታው ለመሳተፊ የሚፈለጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 25 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 2205849/0583208095/ በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

11. ተጫራቾች ያለምንም ስርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ሰነዱ ተቀባይነት ፤ላይኖረው ይቻላል፡ ባጋጣሚ የተሰረዘም ከሆነ የሞላው ድርጅት ፊርማ መኖር አለበት፡፡

12.በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ

Save Tender