የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በ2018ዓ/ም በጀት ዓመት በአውሮፓ ህብረት አደጋ ቅነሳ ፕሮግራም ለፕሮጀክት ጽ/ቤት የሚያገለግል የተለያዩ የኤሌክትሮንክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ከህጋዊ ነጋዴ ድርጅት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ለ3ተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ ጨረታ መስታወቂያ
የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በ2018ዓ/ም በጀት ዓመት በአውሮፓ ህብረት አደጋ ቅነሳ ፕሮግራም ለፕሮጀክት ጽ/ቤት የሚያገለግል የተለያዩ የኤሌክትሮንክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ከህጋዊ ነጋዴ ድርጅት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ:-
1ኛ/በዘርፉ የታደሰ የ2018 ዓ/ም ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2ኛ/የንግድ ምዝገባ ምስከር ወርቀት፡፡
3ኛ/የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
4ኛ/የግብር ከፋይ መለያ TIN ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5ኛ/የ2017ዓ.ም ግብር የከፈሉበት ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል፡፡
6ኛ/ተጫራቾች ከዚህ በፊት በዘርፉ ዕቃያቀረበበት መልካም ሥራ አፈጻጸም ከ2014ዓ.ም ጀምሮ ያለውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
7ኛ/በመንግስት ግዥ ላይ በአቅራቢነት የተመዘገበ ምስከር ወርቀት ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
8ኛ/ተጫራች የሚያስገቡት ነጠላ ዋጋ ለእያንዳንዱ ቫት 15% ያካተተ መሆን አለበት፡፡
9ኛ/ተጫረቾች የጨረታ ዶኮመንት በመግዛት እና በዋጋ ማቅረቢያ በመሙላት ቴከኒካል ኦርጅናል 1፣ፋይናንሻል ኦርጅናል 1 እና ፋይናንሻል ኮፒ 1 በድምሩ 3 ፖስታ ለየብቻ በሰም በማሸግ እና በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅታችሁን ማህተም እና ፊርማ በማድረግ ግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድረስ በማቅረብ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
10ኛ/የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሠነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ ሲሆን ፣ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
11ኛ/ተጫራቾች ዋጋ ስትሞሉ መ/ቤቱ ባዘጋጀው የዋጋ መሙያ መሆን አለበት ካልሆነ ውድቅ ይደረጋል።
12ኛ/በጨረታ ያሸነፈ ድርጅት የውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ከጠቅላላው ዕቃ ዋጋ 10% CPO በኮሚሽኑ ሥም በማስያዝ በ5 ቀን ውስጥ ውል መግባት አለበት፡፡
13ኛ/አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበት ዕቃውን በራሱ ትራንስፖርት እስከ ደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በታርጫ ከተማ በቴሌ በስተጀርባ በሚገኘው ቢሮ ድረስ ማስገባት አለበት፡፡
14ኛ/ተጫራች ጨረታውን ካሳሸጉ በኋላ ያለመገኘት የጨረታ መከፈቻ ሂደቱን እያስተጓጉልም፡፡
15ኛ/የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይንም የበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው በመንግስት ሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
16ኛ/ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00(አንድ መቶ ሺህ ብር) በመ/ቤቱ ሥም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ CPO/ጥሬ ገንዘብ/ በማስያዝ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንት ጋር አሽገው ማቅርብ ይኖርባቸዋል።
17ኛ/ተጫራች የባንከ ጋራንት ደብዳቤ ተቀባይነት የለውም፡፡
18ኛ/ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር/ በባንክ አካውንት 1000521691305 ላይ ገቢ በማድረግ ባንከ አድቫይስ ስታመጡ በ/ደ/ም/ኢ/ህ/ከ/መንግስት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ከግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ርዳይሬከቶሬት በታርጫ ከተማ ከቴሌ ቢሮ በስተጀርባ በምገኘው ቢሮ በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
19ኛ/ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን
