ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችና አገልግሎቶችን መስፈርቱን የሚያሟሉ ብቁ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 004/2018 ዓ.ም
ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችና አገልግሎቶችን መስፈርቱን የሚያሟሉ ብቁ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 - የሀገር አቋራጭ ሞዴስ ZK6122H9 የቶንግ አውቶብስ መለዋወጫ፣
- ሎት 2 - የዩቶንግ አውቶብስ ሞዲስ ZK6116D መለዋወጫ፣
- ሎት 3 - የተለያዩ አነስተኛ ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ እቃዎችን እና
- ሎት 4 - synthetic Transmission oil for Automatic Transmission TE-ML14 and 20
ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር የሥራ ቀናት ለእያንዳንዱ ሎት ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 በአካል በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት በዘርፉ አግባብነት ያለው የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለበትን እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የሚያቀርቡትን የጨረታ ሠነድ ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ሰነድ ኮፒ እና ኦርጅናል በሁለት ፖስታ በማዘጋጀትና በኢንቨሎፕ በማሸግ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ኃላፊነት በተሰጠው አካል ተፈርሞበት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ 2% ሲፒኦ /Bid Bond/ ወይም በባንክ የተመሰከረለት በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ10ኛው ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻው ቀን የዕረፍት ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት ይከፈታል፡፡
- አገልግሎታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከሜክሲኮ ወደ ልደታ ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ላይ ፖሊስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር -011-5-50-45-64
የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት
