Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Trading Businesses Corporation (የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን)
  • Address ደብረዘይት መንገድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114 43 12 76
  • Websitehttps://www.etbc.com.et/index.php/home
  • Deadline17 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price700.00
  • opening date2025-12-17 00:00:00
  • Categories Food Items And Drinks

በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጀስቲከስ አገልግሎት ዘርፍ እሀል፣ የጥራጥሬና የቅባት እህል፣ ሸቀጣሸቀጥ፣ ዘይት፣ ስኳር፣ ቡና እና አትከልትና ፍራፍሬ ምርቶች ግዥ በትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በጨረታ በማወዳደር ግዥዉን መፈጸም ይፈልጋል፡፡


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር፡- ትሎአዘ-ብግጨ 001/2018

በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጀስቲከስ አገልግሎት ዘርፍ እሀል፣ የጥራጥሬና የቅባት እህል፣ ሸቀጣሸቀጥ፣ ዘይት፣ ስኳር፣ ቡና እና አትከልትና ፍራፍሬ ምርቶች ግዥ በትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በጨረታ በማወዳደር ግዥዉን መፈጸም ይፈልጋል፡፡ስለሆነም በጨረታ ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው፡፡

1.የሚፈለገው የተሽከርካሪ ዓይነት

  • ከጅቡቲ ለሚጓጓዙ ምርቶች (ዘይትና ስኳር) ደረጃ 1 ና 2 ድንበር ተሻጋሪ የማጓጓዝ ፍቃድ ያላቸው
  •  በሀገር ውስጥ ለሚጓጓዙ የሀገር ውስጥ የማጓጓዝ ፍቃድ ያላቸው ደረጃ 4 እና ከዛ በላይ
  • የመነሻ እና መዳረሻ ቦታ በጨረታ ሰነድ በተገለፀው መሰረት ይሆናል፡፡

2. ተጫራቶች በዘርፉ ለ2017/2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ/ጨረታው እስከሚከፈትበት ቀን ድረስ ሊያገለግል የሚችል የንግድ ሥራ ፈቃድ የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርቲፊኬት፣ከትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት፡ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ ከሊራንስ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ ምዝገባ ስርተፍኬት (TIN No) ይኖርባቸዋል፡፡ እነዚህ ሰነዶች በቴክኒካል ፕሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ታሽገው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች ከላይ የተገለጹትን ሰነዶች ከጨረታ ሰነድ ማቅረቢያው ቀን ገደብ በፊት ማቅረብ አለባቸው::

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 700.00 (ሰባት መቶ ብር) በመከፈል ከህዳር 22/2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 ሰዓት እንዲሁም ከሰአት ከ7፡30-11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 ሰዓት ድረስ ሀብት አስተዳደርና ግዥ ዋና ክፍል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ::

5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ ታህሳስ 08 /2018 ከጠዋቱ 4፡30 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::

6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 50,000.00 እምሳ ሺህ ብር/ በሲፒአ፣ ጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡ ኢንሹራንስ፣ ቦንድና ቼክ ተቀባይነት የላቸውም፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው በቴክኒካል ፕሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ወይም ለብቻው ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

7. የቴከኒክ ሰነድእናየፋይናንሻል ሰነድ በፖስታ በማሸግናኮፒ እናኦሪጅናል የፋይናንሻል እንዲሁምየቴከኒካል ሰነድ ኮፒዎችን ለየብቻ በፖስታ በማሸግ በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ሁሉንም ፖስታዎች በማድረግ ታህሳስ 08ቀን2018ዓ.ምከጠዋቱ4፡30 ተዘግቶበዚሁዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይምህጋዊወኪሎቻቸው በተገኙበት የትራንስፖርትና ሎጀስቲከስ አገልግሎት ዘርፍ ዋናው መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ አድራሻ ከታች ተገልጿል፡፡

8. አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ መጠን ለአሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10 ፐርሰንት በሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጀስቲከስ አገልግሎት ዘርፍ ስም አሰርተው ውሉን የሚፈጽሙ ይሆናል፡፡

9. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልከ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ስልከ ቁጥር- 251-114 37 92 05 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ

አድራሻ፡ ቃሊቲ መንገድ ቆርኪ ፋብሪካ ፊት ለፊት

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት  

Save Tender