በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የጉምሩክ ኮሚሽን አዲስ አበባ ኤርፓርት ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት በታክስ ዕዳ የያዘውን መኖሪያ ቤት ለመሸጥ ለሦስተኛ ጊዜ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ መ/ቤት ቁጥር 03/2018/
በድጋሚ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የጉምሩክ ኮሚሽን አዲስ አበባ ኤርፓርት ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት በታክስ ዕዳ የያዘውን መኖሪያ ቤት ለመሸጥ ለሦስተኛ ጊዜ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ መ/ቤት ቁጥር 03/2018/
ቅ/ጽ/ቤቱ ስማድል ኮሚውኒኬሽን ተርሚናል ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለአለበት ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመክፈላቸው ምክንያት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 41 በተሠጠው ስልጣን መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 05 መገናኛ አካባቢ አምቼ ፊት ለፊት ለዋና አስፓልት መንገድ በጣም ቅርብ በሆነ ቦታ አክሰስ ሪል እስቴት እና እሳት አደጋ መከላከያ መካከል የሚገኝ የይዞታ ልዩ መለያ ቁጥር AA000060502305 የሆነ G+4 መኖሪያ ቤት ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
- በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራቾች ማንነቱን የሚገልፅ የነዋሪነት መታወቂያ (ፓስፖርት) ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለግልፅ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
|
ተ.ቁ |
የመ/ቤቱ ስም |
ለጨረታ የቀረበው የንብረት ዓይነት |
የንብረቱ መመልከቻ ቀን |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀን |
|
|
አዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት |
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የይዞታ ልዩ መለያ ቁጥር AA000060502305 የሆነ መኖሪያ ቤት |
ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት |
ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 30 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን 8፡00 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ8፡15 ሰዓት ይከፈታል። |
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘውትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት በአዲስ አበባ ኤርፓርት ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ገርጂ ጉምሩክ መጋዘን አስተዳደር ቅጥር ግቢ የዕቃ አወጋገድ ቡድን ቢሮ መውሰድ ይኖርበታል።
- በግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ቤት የሰጡትን ዋጋ 1/10ኛውን ብቻ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በጉምሩክ ኮሚሽን አ/አ/ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት (CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA AIRPORT CUSTOMS BRANCH OFFICE) ስም በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በሚከተለው ጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት ሰነድ ገዝተው መጫረት ይችላሉ።
- የጨረታ መክፈቻ ቦታ:- ገርጂ ጉምሩክ መጋዘን አስተዳደር ቅጥር ግቢ የጨረታ አዳራሽ/የሰራተኞች ካፌ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት/ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
- በግልፅ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 30 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን የመ/ቤቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የግልፅ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ ቀን ይሆናል።
- የጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር እንደ አስፈላጊነቱ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የግልጽ ጨረታ ኮሚቴው መረጃውን አጣርቶ እንደጨረሰ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- የቤት ጨረታ ለሚያሸንፉ ተጫራቾች ከስመ ንብረት ዝውውር ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ወጪዎች ሻጭን አይመለከትም።
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ መ/ቤቱ በሚሰጠው አድራሻ ገቢ በማድረግ ያሸነፉበትን ሃብት ንብረት መረከብ ይኖርባቸዋል።
- ከላይ በተ/ቁ 9 በተገለጽት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ በማድረግ ንበረታቸውን ያልተረከቡ ተጫራቾች የግልፅ ጨራታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በ(CPO) ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ንብረቱ እንዳልተሸጠ ተቆጥሮ በቀጣይ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
- ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ የግልፅ ጨረታን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ስ/ስ/ሼ/ፖ/ጉ/ቅ/ጽ/ቤት
በስልክ ቁጥር 011 668 45 37 እና 011 668 41 93 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ኤርፓርት ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት
