በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው (የህንጻ መሣሪያ) ፌሮ ብረቶችን በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 08/2018 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው (የህንጻ መሣሪያ) ፌሮ ብረቶችን በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዬጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ኘሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-
- ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆነ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የፌሮዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በሥራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት መመልከት ይቻላል፡፡
- 4, በጨረታው ሽያጭ የፌሮው ብረት አስመጪ ቤተሰብ ወይም ባለቤት የሆነ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም፡፡
- በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ምድብ የፌሮ ብረቶች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሰከረለት (CPO) (Customs Adama Branch) ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት በኦንላይን ወይም በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ፡
- በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የወጡት የፌሮ ብረቶች በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ መ/ቤቱ በተከራየው የውርስ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 ጊቢ ውስጥ ስለሚገኙ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በስምንተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ጨረታው ይዘጋል፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን፤ ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 /ሶስት/ የሥራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ የፌሮ ብረቶቹን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ በተ/ቁ 8 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ፌሮው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
- ለጨረታ የቀረቡት የፌሮ ብረቶች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም፡
- ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን፡፡
የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት
በስልክ መስመር 09-05-11-5511 / 011-66-68-828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ለተጨማሪ መረጃ፡-የአዳማ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የውርስ መጋዘን የስራ ሂደት
ስልክ ቁጥሮች-022 111 8429 እና 022 211 8925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ጽ/ቤት
