በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን መ/ቤት በ2018 በጀት አመት ለሚያሰራው መሶብ (የአንድ ማዕከል) አገልግሎት G+6 ህንጻ ግንባታ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ የግንባታ እቃዎች እና የእጅ መሳሪዎችን ማለትም ሲሚንቶ፤ብረት፣ አካፋ፣ዶማ እና ተያያዥ ዕቃዎችን በሎት፡-፣ድንጋይ አሽዋና ጠጠር የመሳሰሉትን በሎት፡-2 የእንጨት አይነቶችን በሎት፡-3፣ዋተር ፓምፕ፣ጀነሬተርየቫይብሬተር ሆዝ፣የፕለይውድ (የጣውላ) መሰንጠቂያ ማሽን እና ተያያዥ ዕቃዎችን በሎት፡-4 እንዲሁም 14M3 Selfe Loading Concrete Mixer በሎት:-5 አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን መ/ቤት በ2018 በጀት አመት ለሚያሰራው መሶብ (የአንድ ማዕከል) አገልግሎት G+6 ህንጻ ግንባታ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ የግንባታ እቃዎች እና የእጅ መሳሪዎችን ማለትም ሲሚንቶ፤ብረት፣ አካፋ፣ዶማ እና ተያያዥ ዕቃዎችን በሎት፡-፣ድንጋይ አሽዋና ጠጠር የመሳሰሉትን በሎት፡-2 የእንጨት አይነቶችን በሎት፡-3፣ዋተር ፓምፕ፣ጀነሬተርየቫይብሬተር ሆዝ፣የፕለይውድ (የጣውላ) መሰንጠቂያ ማሽን እና ተያያዥ ዕቃዎችን በሎት፡-4 እንዲሁም 14M3 Selfe Loading Concrete Mixer በሎት:-5 አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆነን እንገልጻለን፡፡
1. በዘመኑና በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው:
2. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ከገቢውች የተጻፈ ማስረጃ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ _ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃወች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
5. ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ሲሆን ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND) ብር የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በማስላት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዢያ (CPO) በሁኔታ ላይያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ ማቅረብ አለበት፡፡
6. ማንኛውም ተጫራች መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በሚጠይቀው የዋጋ አሞላል ብቻ መሙላት አለበት ፡፡ በሚጠይቀው ዋጋ አሞላል ካልሞሉ የጨረታ ሰነዱ ውድቅ ይሆናል ፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ዝረዝር መግለጫ (ስፔስፊኪሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
8. የጨረታው ውድድር የሚካሄደው በሎት/በጥቅል/ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ አይተም መኖር የለበትም ያልተሞላ አይተም ከተገኘ ከጨረታው ውድቅ ይሆናሉ፡፡
9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር) በመከፈል ከግ/ፋይ/ን/አስ/ደ/ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 508 ማግኘት ይችላሉ፡፡
10. ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ24/3/2018ዓ/ም እስከ 8/4/ 2018 ዓ/ም 11፡30 ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ አንድ ቅጅ ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖሰታ መንገዶች ባለስልጣን መ/ቤት በግዥና/ፋይ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 508 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 9/04/2018 ዓ/ም ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ፋይ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 508 በ 09/04/2018 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ 4፡30 ላይይከፈታል፡፡ ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እሁድና የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻልን ፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13. ለበለጠ መረጃ በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን መ/ቤት አምስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 508 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 033 351 33 37/033 551 05 04/ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ማሳሰቢያ፦
በመ/ቤታችን የተዘጋጀውን ሁሉም ተጫራቾች በተጫራቾች መመሪያ መሰረት የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈጸም ቃል የሚገቡበትን ቅጽ ፈርሞ የድርጅቱን ማህተም በመምታት ጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት አለበት፡፡ የመስሪያ ቤቱ አድራሻ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ህንፃ አምስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 508 ላይ ነው፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን
