በኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን የሸኖ ከተማ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ማረሚያ ቤት ስር የሚገኙ የሕግ ታራሚዎች ጥሬ እህልና የበሰለ ምግብ የተለያዩ ማጣፈጫዎችን እንዲሁም የማገዶ እንጨት ወይም የምግብ አቅርቦት ከ01/05/2018ዓ.ም ጀምሮ እስከ 30/04/2019 የሚቆይ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን የሸኖ ከተማ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ማረሚያ ቤት ስር የሚገኙ የሕግ ታራሚዎች ጥሬ እህልና የበሰለ ምግብ የተለያዩ ማጣፈጫዎችን እንዲሁም የማገዶ እንጨት ወይም የምግብ አቅርቦት ከ01/05/2018ዓ.ም ጀምሮ እስከ 30/04/2019 የሚቆይ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ማንኛውም ጨረታውን ለመካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ፡-
- የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ወይም ቢሮ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የ2018ዓ.ም የሥራ ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና አግባብነት ያለው የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- አቅራቢዎች የሸኖ ካተማ ማረሚያ ቤት በሚገኝበት ሸኖ ከተማ ውስጥ ለምግብ እህል ክምችት የሚያገለግሉ መጋዘን ያላቸው ወይም የበሰለ የምግብ አቅርቦት ማዘጋጀት የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በከተማ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ጽ/ቤት መቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በከተማ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያውን ከመቶ ሁለት (2 ፐርሰንት) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ CPO" እና የእህሉን ናሙና ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው።
- በጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ተደራጅተው የበሰለ ምግብ ለማቅረብ የሚቀርቡ ማህበራት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ ይቆያል፡፡ በ16ኛ ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሰዓት በሻኖ ከተማ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም የሕግ ታራሚ ኮሚቴዎችና የመ/ቤቱ የጨረታ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ይከፈታል።
- መ/ቤቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ውሉን የማስዥ መሆኑን ሙሉ በሙሉ የማቋረጥ መብት አለው።
- ተጫራቾች የምግብ እህሉንም ሆነ ማጣፈጫዎችን እና የማገዶ እንጨት በራሳቸው ማጓጓዣ ወጪ እስክ ማረሚያ ቤት ድረስ ማቅረብ ወይም የበሰለ ምግብ ማዘጋጀት የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ምግብ የሚበስለው በማረሚያ ቤት ውስጥ በተዘጋጀ ማብሰያ ቤት ውስጥ ሆኖ የማብሰያ ዕቃ በመ/ቤቱ የሚቀርበው እንዳለ ሆኖ በቂ ዕቃ በሌለበት ከራሱ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
- በጥቃቅንና አነስተኛ መደራጀታቸውን የሚገልጽ ከጥቃቅንና አነስተኛ አደራጅ ጽ/ቤት ማረጋገጫ ያላቸው።
አድራሻ፡- ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው መንገድ 78 ኪሎ ሜትር ሸኖ ከተማ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0116870021/0922464820 በመደወል ጠይቆ መረዳት ይቻላል።
በኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን የሸኖ ከተማ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ጽ/ቤት
