በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሐርረጌ ቅ/ጽ/ቤት ጀሎ ሙክታር፣ ጋራ ሙለታ፣ ጃርሶ ጉርሱም፣ እና ዲንዲን ዲስትሪክት ላይ የቁም ባህርዛፍ ግንድላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር OFWEDH/GUO 02/2018
በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሐርረጌ ቅ/ጽ/ቤት ጀሎ ሙክታር፣ ጋራ ሙለታ፣ ጃርሶ ጉርሱም፣ እና ዲንዲን ዲስትሪክት ላይ የቁም ባህርዛፍ ግንድላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
- የግንድላ እና የአጠና፣ እንጨት መሰንጠቂያ ወይም ተዛማጅ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የቫት (VAT) ተመዝጋቢና “TIN number” ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ጭሮ ከተማ ም/ሐረርጌ ዞን እና ኢነርጂ ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ከሐርረጌ ቅ/ጽ/ቤት በመግዛት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል።
- ጨረታው የሚዘጋበትና የሚከፈትበት ቀንና ሰአት ጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል።
- ተጫራቾች (የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% ጭሮ ከተማ ውስጥ በሚገኙት ባንኮች በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 025 551 2767 / 025 551 2239 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሐረርጌ ቅርንጫፍ
