የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በእዣ ወረዳ በዳርቻና አጓጅተረህ ቀበሌ ውስጥ የሚገኝ የአቡሴ የባህር ዛፍ ደን ሽያጭ በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በእዣ ወረዳ በዳርቻና አጓጅተረህ ቀበሌ ውስጥ የሚገኝ የአቡሴ የባህር ዛፍ ደን ሽያጭ በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ፡-
1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ሰው ወይም ድርጅት የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በጉ/ዞን ገቢዎች መምሪያ በመክፈል ሰነዱን ከጉራጌ ዞን ፋይናንሰ መምሪያ ግ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 18 መውሰድ ይችላሉ። ሰነዱ በዞኑ ፋይናንስ መምሪያ የሚሸጠው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ይሆናል።
2. የደኑን ሁኔታ ለመጎብኘት ይህ የሽያጭ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ12ኛው እና 13ኛው ቀናት በአካል ለማየት የሚፈልግ ተጫራች በመምሪያው ተመዝግቦ መምሪያው ከሚመድበው ባለሙያ ጋር በመሄድ አስፈላጊውን መረጃ ማግኘት ይችላል።
3. የጨረታ ሽያጩ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመምሪያው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር ብቻ/ በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ስም በተዘጋጀ ሲ.ፒ.ኦ/ቢድ ቦንድ የጨረታ ሽያጭ ሣጥኑ ከመከፈቱ በፊት ወይም ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ዋጋ የጨረታ ውጤት በሚመለከተው አካል ፀድቆ በማስታወቂያ እንዲከፈል ከተነገራቸው በኋላ በአራት ዙር ከፍለው ማጠናቀቅ አለባቸው።
6. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ በመንተራስ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
7. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ግለሰብ አሸናፊነቱ በሚመለከተው አካል መፅደቁ በማስታወቂያ ከተገለፀለት ከ5 ቀን በኋላ ከመምሪያው/ከሻጭ/ ጋር የሽያጭ ውል መፈራረም አለበት።
8. በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ /ቢድ ቦንድ/ የጨረታ ሽያጭ ለአሸናፊው በሚመለከተው አካል መፅደቁ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ የሚመለስላቸው ይሆናል።
9. ተጫራች አሸናፊነቱን ባወቀ በ4 ወር ጊዜ ውስጥ የደኑን ውጤቶች ሙሉ በሙሉ አንስቶ መጨረስ ይኖርበታል።
10. ተጫራች አሸናፊነቱን ባወቀ በ3 ወር ጊዜ ውስጥ በአራት ጊዜ ክፍያ ያሸነፈበትን ገንዘብ አጠቃሎ ገቢ እንዲያደርግና ባያደርግ ያስያዘውን የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ በማድረግ ጨረታው ተሰርዞ ሌላ ጨረታ መምሪያው ማውጣት ይችላል።
11. መምሪያው በሽያጩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይተላለፋል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-330-0112 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ
የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
