በአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ አስመልክቶ ስፋቱ 175 ካሬሜትር የሆነ ቤት እና ቦታ ለእዳ ማስፈፀሚያ እንዲውል በመነሻ ዋጋ በብር 2,236,203.92 /ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰላሳ ስድስት ሺህ ሁለት መቶ ሶስት ብር ከዘጠና ሁለት ሳንቲም/ በጨረታ ስለሚሸጥ ስለሆነም መግዛት የምትፈልጉ ግለሰቦች በጨረታው እንድትወዳደሩ የመቐለ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት አዟል ፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ከሳሽ :- አዋሽ ድንበር ተሻጋሪ ደረጃ 4 የደረቅ ጭነት ማመላለሻ የግል ድርጅት
አድራሻ መቐለ ከተማ ሰሜን ክ/ከተማ
ተከሳሾች፡-
-
- አቶ አዲሱ ገ/ሄር ፣
- ወ/ሮ አልጋነሽ ነጋሽ ፣
መካከል ባለው የአፈፃፀም ክርከር በዓብይ ዓዲ ከተማ ቀበሌ 03 ዶክተር አታክልቲ ቀጠና የሚገኝ አዋሳኙ በምስራቅ መንገድ ፣ በምእራብ ድምፁ ሃይሉ በሰሜን ሓፈሱ በድሩ በደቡብ ክፍት ቦታ ስፋቱ 175 ካሬሜትር ፣ ፋይል ቁጥሩ 2089 የሆነ በ 2ኛ አፈፃፀም ተከሳሽ በወ/ሮ አልጋነሽ ነጋሽ ስም የሚታወቅ ቤት እና ቦታ ለእዳ ማስፈፀሚያ እንዲውል በመነሻ ዋጋ በብር 2,236,203.92 /ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰላሳ ስድስት ሺህ ሁለት መቶ ሶስት ብር ከዘጠና ሁለት ሳንቲም/ በጨረታ ስለሚሸጥ የጨረታ አሸናፊ ጨረታው በተደረገበት ቀን የጠቅላላ ዋጋ 25% በጨረታው ቀን የሚያስይዝ ቀሪው ሙሉ ክፍያ ደግሞ በ15 ቀናት ውስጥ ሊከፍል የሚችል ጨረታው የሚካሄደው በተገለፀው ቤት እና ቦታ በ04/5/2018 ዓ/ም ከ3፡00- 6:00 ሰአት ሲሆን የጨረታው ውጤት የሚገለፀውም በ05/5/2018 ዓ/ም 3፡00 ሰዓት ችሎት ላይ መሆኑን አውቆ እንዲጫረት የመቐለ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት አዟል ፡፡
በትግራይ ብ/ክ/መንግሥት የመቐለ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት
