የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት እንጦጦ ላይ ባስገነባዉ አዲሱ የአትሌቲክስ መንደር ዉስጥ ለሚገኙና ብዛታቸዉ 46 ለሚሆኑ አትሌቶችና አሠልጣኞቻቸዉ በጨረታ ሰነዱ ዉስጥ በተዘረዘረዉ መሰረት በዚየዉ ካምፕ ዉስጥ በመቀመጥ የምግብ አገልግሎት የሚሰጡ ሆቴሎች፤ ድርጅቶች ማህበራትና ግለሰቦችን በጨረታ አወዳድሮ ለ6 ወር ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
የአትሌቶች የምግብ አቅርቦት ግዥ ጨረታ
ጨረታ ቁጥር፣ ኦ.ደ.ዱ.እ.ድ -04/2018
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት እንጦጦ ላይ ባስገነባዉ አዲሱ የአትሌቲክስ መንደር ዉስጥ ለሚገኙና ብዛታቸዉ 46 ለሚሆኑ አትሌቶችና አሠልጣኞቻቸዉ በጨረታ ሰነዱ ዉስጥ በተዘረዘረዉ መሰረት በዚየዉ ካምፕ ዉስጥ በመቀመጥ የምግብ አገልግሎት የሚሰጡ ሆቴሎች፤ ድርጅቶች ማህበራትና ግለሰቦችን በጨረታ አወዳድሮ ለ6 ወር ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡-
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸዉና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ታክስ ክሊራንስ ያላቸዉ በጨረታዉ ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል፤ አዲስ አበባ ከተማ ቀበና አይል ሊቢያ አጠገብ ከሚገኘዉ የድርጅቱ ቢሮ 4ኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘዉ ቢሮ ቁጥር 401 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸዉን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ማቅረብና ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሣጥን ዉስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ ታህሳስ 14 ቀን 2018ዓ/ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ከላይ በተገለጸዉ አድራሻ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) የሚሆን ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ወይም አዲስ አበባ ዉስጥ ከሚገኙ ባንኮች በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND GURANTEE) በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ስም ቢያንስ ለ 90 ቀናት የሚያገለግል አዘጋጅቶ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች አንዱ ተጫራች ባቀረበዉ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ከታች የተገለጸዉን ስልክ ቁጥር በመደወል ወይም በፋክስ በጽሑፍ መጠየቅና ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
አድራሻ አዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር፤ አራዳ ክ/ከተማ፤ ወረዳ 07፤ ቀበና አይል ሊቢያ አጠገብ
ስልክ ቁ. 011-122-00-20/84/011-124-02-58
ፋክስ ቁ. 011-124-64-55
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
