በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊሲ ኮሚሽን በጎፋ ዞን የሣውላ ማረሚያ ተቋም ከጥር 1 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረሰ ለ6 ወራት በህግ ጥላ ስር በመታረም ላይ ለሚገኙ ለህግ ታራሚዎች ምግብና አገልግሎት የሚውል፡- እህል ማጣፈጫ ቅመማቅመም፣ ንፁህ የምግብ ዘይት ሰኳር እና የማገዶ እንጨት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊሲ ኮሚሽን በጎፋ ዞን የሣውላ ማረሚያ ተቋም ከጥር 1 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረሰ ለ6 ወራት በህግ ጥላ ስር በመታረም ላይ ለሚገኙ ለህግ ታራሚዎች ምግብና አገልግሎት የሚውል፡- እህል ማጣፈጫ ቅመማቅመም፣ ንፁህ የምግብ ዘይት ሰኳር እና የማገዶ እንጨት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያለው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈለ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ
- የግብር መለያ Tin ቁጥር ያለው
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወርቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ቼክ በCpo እና በጥሬ ገንዘብ የተረጋገጠ 25,000 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከ1 እስከ 5 የተጠቀሰዉን ማስረጃዎችን እና የማጫረቻ ሠነድ ኦርጅናልና ኮፕ በተለያዩ ፖስታ ውስጥ በማስገባት በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በመንግስት የሥራ ሰዓት ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመንግስት የሥራ ስዓት ቢሮ ቁጥር 9 በመቅረብ የማይመለስ 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሠነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች ዕቃውን በራሳቸው ወጪ እስከ ሣውላ ማረሚያ ተቋም አምጥተው ማስረከብ አለባቸው።
- የጨረታው አሸናፊ ሆኖ የተገኙ ተጫራች የዕቃዎችን አጠቃላይ ዋጋ በ10% በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም /Cpo/ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከሣውላ ማረሚያ ተቋም ግዥ ፋ/ን/አስ/ር ደጋፊ ሥራ ሂደት ጋር የውል ስምምነት መፈፀም ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀን ከሁሉም እሀልና ማጣፈጫ ዓይነት ናሙና ይዘው መቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ማሰታወቂያ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሳጥን 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ ዕለቱ ቅዳሜ ፤ እሁድ እና በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በመንግስት ሥራ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መወዳደር ተቀባይነት የለውም፡፡
- ማረሚያ ተቋሙ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ 0467770041/0467770501
የሣውላ ማረሚያ ተቋም የግዥ ፋ/ን/አስ/ር ደጋፊ ሥራ ሂደት
