የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት ለተለያዩ የከባድ ማሸነሪዎችና ተሸከርካሪዎች መለዋወጫ ዕቃዎችና ለመግዛት የቄራ መኪናዎች የቦድ ዕድሳትና ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ያስፈለገ በመሆኑ በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት ለተለያዩ የከባድ ማሸነሪዎችና ተሸከርካሪዎች መለዋወጫ ዕቃዎችና ለመግዛት የቄራ መኪናዎች የቦድ ዕድሳትና ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ያስፈለገ በመሆኑ በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት፡-
- የከባድ ተሽከርካር መኪና፣ ሎት /ምድብ 1(አንድ)
- የከባድ ማሽነሪዎች፣ ሎት/ምድብ 2(ሁለት)
- የቀላል /መለስተኛ መኪናዎች ሎት ምድብ 3(ሶስት)
- ለተለያዩ ለከባድ ተሽከርካሪዎች ማሸነሪዎች ለቀላል መለስተኛ መኪናዎች የሚሆን ባትሪ በተለያዩ አምፕር፣ ሎት ምድብ 4 (አራት)
- የቄራ መኪናዎች የቦድ ዕድሳትና ጥገና
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡-
- በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ
- የእቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው ፣
- የዘመኑን የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንከ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /ለአስር/ ተከታታይ ቀናት በመጠቀም ብር 400 /አራት መቶ/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ አርጅናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም በፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ11ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪለቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፣ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና /ኢኮ/ልማት መምሪያ
ሀዋሳ
