የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ የቡና ጆንያ (Coffee Sack)፣ የቡና ኤክስፖርት ከረጢት (Coffee Export bag) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር OSE/NCB/011/2018
የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ
ሎት 1. የቡና ጆንያ (Coffee Sack) (ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ)
ሎት 2. የቡና ኤክስፖርት ከረጢት (Coffee Export bag) (ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም አስፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች፡-
- የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት
- የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No)
- የአቅራቢነት ማስረጃ (Suppliers List)
- የሚፈለግባቸውን የመንግሥት ግብር ስለመወጣታቸው የሚገልጽ ማስረጃ፣ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።
ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ፡- ለ15 ተከታታይ ቀናት ሰነዱን በመግዛት በ16ኛው የሥራ ቀን ጨረታው የሚዘጋና የሚከፈት ይሆናል። የጨረታ ሰነድ መግዣ ዋጋ ብር 200 (ሁለት መቶ) መሆኑን እየገለጽን፤ ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን በፖስታ በማሸግ በተጠቀሱት ቀናት ከጠዋቱ 2:30-8፡00 ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት በጨረታው እንዲትሳተፉ እንጋብዛለን።
የጨረታ ሳጥኑ ከላይ በተጠቀሱት ቀናት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንተርፕራይዙ ዋና መ/ቤት ጎተራ አጎና ሠራዊት ሲኒማ አጠገብ ባለኬር ህንፃ /Baleker Tower/ 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 402 ይከፈታል።
ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢንተርፕራይዙ የሥራ ሰዓት ከሰኞ-አርብ ጠዋት ከ2፡30-6፡30 ከሰዓት በኋላ ከ7፡30- 11፡30 ነው።
ለበለጠ ማብራሪያ፡-
ስ.ቁ፡- 011-416 0309/ 011-466-2527 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ
