Tender Detail

Tender Details

  • Company የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
  • Address ከሚሴ ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 033 554 02-55
  • Website
  • Deadline30 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2025-12-30 00:00:00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በከሚሴ ከተማ አስተዳደር የከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽህፈት ቤት ለመኖሪያና ድርጅት አገልግሎት የሚውሉ የልማት ቦታዎችን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል


የ2018 ዓ.ም 1ኛ ዙር የሊዝ

ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በከሚሴ ከተማ አስተዳደር የከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በከሚሴ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ለድርጅት 4,453.09 ካ.ሜ እና ለመኖሪያ 362.61 ካሜ ጠቅላላ ስፋታቸው 4,815.7 ካሬ ሜትር የሆኑ ለመኖሪያና ድርጅት አገልግሎት የሚውሉ የልማት ቦታዎችን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል።

በዚህም መሰፈረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች

  1. የጨረታውን ሰነድ በከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ሸያጭ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
  2. ተጫራቶች ቦታዎቹ የሚገኙበት ድረስ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎቹን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ።
  3. ተጫራቶች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቶች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው ስፔስፊኬሽን / Specification/ መሰረት መሆን ይኖርበታል፡ተጫራቶች በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ቦታ ስፋት በሊዝ መነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 20 በመቶ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ/ CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይም ከ 20 ከመቶ ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል፡፡ እንዲሁም አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
  4. ተጫራቾች የቅድመ ክፍያ ከጠቅላላው ብር ላይ 30% መክፈል የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
  5. የጨረታ አሸናፊወችን ለመለየት የሚከተሉትን የማወዳደሪያ መስፈርቶችን መሰረት በማድረግ ይሆናል።
  1. ሀ) ተጫራቾች ለቦታው ያቀረቡት ዋጋ 80%
  2. ለ) የሊዝ ቅድመ ክፍያ መጠን 30% የሚያዝ ይሆናል
  1. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ፣ ሲፒኦ እና ሌሎች የጨረታ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብክመ በከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ በወጣበት ቀን ከ 07/04/2018 እስከ 20/ 04 / 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  2. ጨረታው የሚዘጋበት ቀን በ20/4/2018 ዓ.ም 10፡30 ሰዓት ይሆናል።
  3. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ 21/4/2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት በከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት አዳራሽ ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  4. በጋራ ተደራጅተው /በአክሲዮን/ እነ በሚል ሰነድ ለመግዛት የሚፈልጉ አካላት ከሚመለከተው አካል እነ የተባላችሁበትን ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ መረጃ በስም ዝርዝር ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  5. ቦታውን ለመጎበኘት ለሚፈልጉ ተጫራቶች ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ለሽያጭ የተዘጋጁ ቦታዎች በሚገኙበት የከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በሚመድባቸው አስጎብኝዎች ቦታዎቹን መመልከት ይችላሉ።
  6. የአካበቢውን ወቅታዊ የሊዝ ጨረታ መነሻ ዋጋ እና ሌሎች የከተማ መሬትን በሊዝ ለማስተዳደር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በማድረግ በከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መመልከት ይችላሉ።
  7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ፡-

በስልክ ቁጥሮች 0913 501 899/ 033 554 0255/0913 259 920 ወይም

Gmail address Ke.ketemaaglglot@gmail.com .መጠየቅ ይችላሉ።

 

የከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ / ቤት

Save Tender