Tender Detail

Tender Details


የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩከ ቅ/ፅ/ቤት በ11/04/2018 ዓ/ም በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩከ ቅ/ፅ/ቤት በ11/04/2018 ዓ/ም በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት መግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት በተጫራች ስም የማይመለስ 100(መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ፣ ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት፣እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣልዎት የምትፈልጉት የእቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት እንዲመጣልዎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

የጨረታ መስፈርቶች

  1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልግ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለ መሆኑ ክሊራንሰ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅሰቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት፣በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል።
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀን 11/04/2018 ዓ/ም ባሉት ቀናት በግልፅ እስከ ጠዋቱ 3፡45 እንዲሁም ሐራጅ ጨረታ በዚሁ ቀን እስከ ረፋዱ 5፡00 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ ።
  3. ለግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (cpo) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5% እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጨራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ።

የጨረታ ቦታ

የጨረታ ዓይነት

 

ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች

 

የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

ቃሊቲ ጉምሩክ

 

ግልጽ እና ሐራጅ

 

ጫማዎች፡አልባሳት፡ ኮስሞቲክስ፡ የመኪና መለዋወጫ፤ ኤሌክትሮኒክስ፡የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ፡ምግብነክ፡  ረኮ ቦት እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች

ለግልፅ ጨረታ እስክ 11/04/18 ቅዳሜ ጠዋቱ 3:45 እና ለሐራጅ ጨረታ እስክ 4:45

ለግልፅ ጨረታ 11/04/18 ጠዋቱ 3፡45 እና ለሐራጅ ጨረታ እስከ 5:00

 

 

  1. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- በቃሊቲ ጉ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
  2. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋሰትና ያስያዙት (cope) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የሥራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  3. ከአሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውሰጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖርበታል፡፡
  4. ከላይ በተ.ቁ.7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሜ ለሽያጭ ይቀርባል።
  5. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ጉምሩክ ኮሚሽን አዋሽ ቅ/ፅቤት

Save Tender