Tender Detail

Tender Details

  • Company ADDIS ABEBA CITY BUS SERVICE ENTERPRICE (የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት)
  • Address 22 ኢየሩስ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251118212214
  • Website
  • Deadline30 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2025-12-30 00:00:00
  • Categories Vehicle Spare Parts

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ በግዥ መለያ ቁጥር አእከአአድ/ብግጨቁ/019/2018 ቪዝ ግላስ (Viz Glass) የሚቆረጥ መስታወት ለአውቶቡስ አገልግሎት የሚውል አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ በግዥ መለያ ቁጥር አእከአአድ/ብግጨቁ/019/2018 ቪዝ ግላስ (Viz Glass) የሚቆረጥ መስታወት ለአውቶቡስ አገልግሎት የሚውል አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በመስኩ የተሰማሩና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፡-

1. በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኮፒ (Valid Trade licensee)

2. በመንግስት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የአቅራቢዎች ዝርዘር ውስጥ ስለመግባቱ በድረ-ገፅ የተመዘገበበት

3. የታከስ ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣

4. የተጨማሪ እሴት ታከስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ (VAT Certificate) ፣

5. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ፈቃድ (Valid Tax Clearance Certificate)!

6, የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) በማቅረብ በግልፅ ጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ፡፡

በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ እስከ ምሳ ሰዓት (6፡00 ሰዓት) የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመከፈል በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 22 እየሩስ ህንጻ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት (ማዕከል) የግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ወይም 7-01 መውሰድ ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቴከኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ በመለየት እስከ ታህሳስ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ በግዥ ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር7-02 ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው ታህሳስ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ጠዋት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በግዥ ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ!

ድርጅቱ የተሻስ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ

የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር: 0118 21 22 14

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ

አገልግሎት ድርጅት

Save Tender