የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የሚያገለግል የበር መቆለፊያ ተንጠልጣይ ቁልፍ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የበር መቆለፊያ ተንጠልጣይ ቁልፍ ግዥ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር NEBE/NCB/09/2018
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የሚያገለግል የበር መቆለፊያ ተንጠልጣይ ቁልፍ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ታኅሣሥ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 እና ከ7፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከቦርዱ ግዥ ስራ ከፍል ቢሮ ቁጥር 107 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ምዝገባ ምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እንዲሁም በመንግሥት የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ድህረ-ገጽ የአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ ስለመሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታ ሰነዱን ከቦርዱ ዋና መስሪያ ቤት የግዥ አስተዳደር የስራ ክፍል በመውሰድ ሞልተው አግባብ ባለው አካል በመፈረም ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን የቴክኒክና የዋጋ ሰነዳቸውን ኦርጅናልና ኮፒ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያነት ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ታህሳስ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
- ቦርዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በአካል ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አድራሻ ቦሌ መንገድ ፍላሚንጎ ሬስቶራንት ገባ ብሎ ካለው ዋና መ/ ቤት በመቅረብ መጠየቅ ይችላል።
አድራሻችን፡- ቦሌ ፍላሚንጎ ካፌ ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡- +251 115153468
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
