Tender Detail

Tender Details

  • Company በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙ ገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline22 Sep 2026, 9:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 575.00
  • opening date መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Categories Personal Protective Safety Equipment

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል የእሣት ማጥፊያ መሣሪያዎች ፍተሻና ሙሌት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል ገብቶ ማሠራት መግዛት ይፈልጋል፡፡


የሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ሙሲፋ/23/2018

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል የእሣት ማጥፊያ መሣሪያዎች ፍተሻና ሙሌት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል ገብቶ ማሠራት መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የ2018/2019 ዓ/ም የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የታክስ ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት ገርጂ የቀድሞው ኤምፔሪያል ህንፃ ከሚገኘው የፋብሪካው የግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዕለቱ መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡

ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ

አዲስ አበባ

Save Tender