በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለደሴ ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለሥልጣን አገልግሎት የሚውሉ ነገሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በነጠላ ዋጋ ውድድር መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 02/2018
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለደሴ ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለሥልጣን አገልግሎት የሚውል
- የተለያዩ የኮንስትራክሽን ተሽከርካሪና ማሽነሪዎች ኪራይ (ተጫራቹ የኦፕሬተር አበል፣ የነዳጅ፣ የቅባት፣ ዘይትና ሌሎች ወጪዎችን ችሎ)
- የሕንፃ መሣሪያ፣
- ቢትመን 60/70
- ጀኔሬተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በነጠላ ዋጋ ውድድር መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የተሰጠ ወይም የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።
- የግዥ መጠን ከብር 200,000 በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- የሚቀርቡት የኮንስትራከሽን ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች ኪራይ በሙሉ የፈረስ ጉልበታቸው፣ የስሪት ዘመናቸውና ሌሎች በጨረታ ሰነዱ የተገለጹ መስፈርቶች ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ኮፒ አያይዘው ማስገባት አለባቸው፡፡ የፈረስ ጉልበታቸውና የስሪት ዘመናቸውን መረጃ ያላያያዘ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይደረጋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 2% ከነቫቱ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ እሰከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰአት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘ ተጫራች የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የሌለውም፡፡
- የመጫረቻ ሰነዱ /የጨረታ ሰነዱ/ ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ ለ40 ቀን /አርባ ቀን/ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለተጨማሪ 30 ቀናት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ብቻ በመክፈል ደሴ ከተማ አስ/መንገዶች ባለሥልጣን ግዥና ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስ/ሂደት ማግኘት ይቻላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሣቡን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ ደሴ ከተማ አስ/መንገድ ባለሥልጣን ከግዥና ፋ/ንብ/አስ/የስ/ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን እስከ ቀኑ 11፡30 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል በዚሁ ሰዓት ይታሸጋል።
- ማንኛውም ተጫራቾች ያቀረበው የጨረታ ሰነድ ፖስታው ሲከፈት የጨረታ ማስከበሪያ ወይም ሲፒኦ የሌለው ወይም የጨረታ ማስከበሪያው የሚያንስ ከሆነ በጨረታ ሰነዱ ላይ የሞላው ዋጋ የማይነበብና ተጫራቹም ከጨረታ ውድድር ውጭ የሚሆን መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ መሙላት የሚችሉት መ/ቤቱ ባዘጋጀው የዋጋ መሙሊያ ሰነድ ብቻ ሲሆን በሌላ ወይም በራሱ የዋጋ መሙሊያ ሞልቶ ቢያቀርብ ተጫራቹን ከውድድር ውጭ የሚደርግ ይሆናል።
- በጨረታ በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ሙሉ ስማቸውን፣ ፊርማና የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡ በተጨማሪም በዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከሆነ ከውድድር ውጪ ያስደርጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደሴ ከተማ አስ/መንገዶች ባለሥልጣን መ/ቤት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሠዓት ይከፈታል፡፡ የሚከፈትበት ቀን የበዓላት ቀን ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ /ማሸነሪ/ ደሴ ከተማ አስ/መንገድ ባለሥልጣን መ/ቤት ድረስ በራሱ ማጓጓዥ ማስጫኛ እና ማውረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በነጠላ ዋጋ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 312 91 72/ 033 311 10 41/10 48/10 59 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- ካራጉቱ መስጅድ ፊት ለፊት
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለደሴ ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለሥልጣን አገልግሎት
