የኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፈዴሬሽን ኃላ.የተ እሰላ ብቅል ፋብሪካ ጥራትና ደረጃውን የጠበቁ የተለያዩ የብቅል ምርት ማሸጊያ ከረጢት፣ ተረፈ-ምርት መቋጠሪያ ከረጢት፣ የተበጠረ ገብስ መቋጠሪያ ከረጢት እና የእንስሳት መኖ ማሸጊያ ከረጢት አቅም እና ፍላጎት ያላቸውን አምራች ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: NCB/OACFLTD/AMF/14/2018
የኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፈዴሬሽን ኃላ.የተ እሰላ ብቅል ፋብሪካ ጥራትና ደረጃውን የጠበቁ የተለያዩ የብቅል ምርት ማሸጊያ ከረጢት፣ ተረፈ-ምርት መቋጠሪያ ከረጢት፣ የተበጠረ ገብስ መቋጠሪያ ከረጢት እና የእንስሳት መኖ ማሸጊያ ከረጢት አቅም እና ፍላጎት ያላቸውን አምራች ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።
- ተጫራቾች የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝርውስጥ የተመዘገቡ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በፋብሪካችን አካውንት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000257808697 ወይም በአሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ 1000043405229 በመክፈል/ገቢ በማድረግ)።
- ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ጠዋት 2፡00-6፡00 ከሰዓት በኋላ 7፡00-10፡00 ሰዓት ድረስ ከጀርመን አደባባይ ወደ ሚካኤል አደባባይ በሚወስደው መንገድ ላይ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው የአሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን ሕንፃ ስድስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 ወይም አሰላ-ቁሉምሳ ከሚገኘው ፋብሪካችን ቢሮ ቁጥር 003 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በፖስታ በማሸግ አዲስ አበባ በሚገኘው የፋብሪካችን ዋና መ/ቤት በኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን ኃላ.የተ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ከታች ከተጠቀሰው የመዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ወይም Bank Guarantee ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የፋይናንሽያል እና ቴክኒካል ፖስታቸውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ በተቀመጠው ዝርዝር መስፈርት መስረት ሶስት ናሙና ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን፡-
- ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ለመገኘት በሚሹ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው የፋብሪካችን ዋና መ/ቤት የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ/የተ 7ኛ ፎቆ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች በጨረታ ማስታወቂያና በተጫራቾች መመሪያ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነጥብ ካለና ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡- 09-65-65-04-81/09-65-65-02-85 በሥራ ሰዓት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኦሮሚያ ግብርና ኀብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ.የተ አሰላ ብቅል ፋብሪካ
