የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የክሬን፣ ፎርክሊፍት፣ ሎቤድና ተያያዥ የተሽከርካሪ እና የተሽከርካሪ ማሽነሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በግልፅ ጨረታ ቁጥር ቤ/ል/ኮ/ግ/ጨ/007/2018
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የክሬን፣ ፎርክሊፍት፣ ሎቤድና ተያያዥ የተሽከርካሪ እና የተሽከርካሪ ማሽነሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በዘርፉ /2018 የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ እና ንግድ ምዝገባ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በድረ ገፅ /Online/ የተመዘገቡ ማስረጃቸውን ኮፒና ኦርጅናል አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ቂርቆስ ከ/ከተማ ወረዳ 01 ባንቢስ አካባቢ ግሪክ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ያለው ህንፃ ላይ 4ተኛ ፎቅ በኮርፖሬሽኑ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን በግልፅ ጨረታ ቁጥር ቤ/ል/ኮ/ግ/ጨ/007/2018 ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይንም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው ታህሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ 9ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 901 ይከፈታል፡፡ ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ባንቢስ አካባቢ ግሪክ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የቤቶች ልማት ህንፃ
ስልክ ቁጥር፡- 0936-99-35-20/0911-82-03-59
በቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን
