መ/ቤታችን የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በሥሩ ላሉት ዲስትሪክቶች አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን እና ኢንጅነሪንግ መሣሪያዎች መገልገያ ማለትም የግልባጭ መኪና እስከነ ሎደሩ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ደኢመባ 07/18
መ/ቤታችን የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በሥሩ ላሉት ዲስትሪክቶች አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን እና ኢንጅነሪንግ መሣሪያዎች መገልገያ ማለትም የግልባጭ መኪና እስከነ ሎደሩ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
በመሆኑም፣
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈሉበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ የፋይናንሻል ፕሮፖዛሉን በተለያየ ፖስታ በማድረግ እንድ ዋና እና እንድ ኮፒ ኦሪጂናል እና ኮፒ በማለት እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያው ኦሪጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ለብቻው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር ብቻ/ በመክፍል ከባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት የቢሮ ቁጥር 05 መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው፤
- አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ድረስ ይሆናል። ጨረታው በዚያ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ መንገድ ብር 40,000.00 /አርባ ሺህ ብር ብቻ/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በግዥ መመሪያው ላይ በተፈቀደ አቅራቢው በሚፈልገው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።
የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን
አቅ/ን/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት
የፖስታ ሳጥን ቁጥር 404
ስልክ ቁጥር 0461315012/0932708847/0923690085
ዲላ ኢትዮጵያ
የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን
