የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለብዙኃን ቅስቀሳ አገልግሎት የሚውል ሞንታርቮና ሜጋፎን ስፒከር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
ለሞንታርቮ እና ለሜጋፎን ስፒከር ግዥ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለብዙኃን ቅስቀሳ አገልግሎት የሚውል ሞንታርቮና ሜጋፎን ስፒከር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ሀ. ሚንታርቮ
Montarbo B112 (12" Active 2-way Speaker, 1200W Peak, Bluetooth 5.0, 3-ch mixer.)
ለ. ሜጋፎን ስፒአር
Compact Handheld (20W 25W) Power: 20-25W Peak; Range: 400-600 yards; Features: Built-in Siren, Volume Control, Foldable Handle, ABS Body Hand strap, 4-8 AA/D batteries (or rechargeable pack).
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በዘርፉ የተሰማሩ የዘመኑ የመንግስት ግብር የከፈሉ ወይም የ2018 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያደሱ ፣ በጨረታው መሳተፍ የሚያስችል ከገቢዎች ክሊራንስ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ እና የግብርመለያ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አንዱ ተጫራች በሌላዉ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት ከጨረታዉ የሚያሳግድ ይሆናል።
- ተጫራቾች ከጨረታው በኋላ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድቦንድ ለሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ (2%) በCPO ወይም ባንክ ጋራንቲ አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር መሆኑን ወይም አለመሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራች ጨረታውን በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስራ አምስት (15) የስራ ቀናት ውስጥ ጨረታ ሰነዱን በጉርድ ሾላ ሳሊህተ ምህረት ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ድራር ሞል አጠገብ ከሚገኘዉ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመገኘት የጨረታዉን ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ በብር (800) ብር (ስምንት መቶ ብር) በመግዛት የጨረታ ሰነዳችሁን እስከ ታህሳስ 30/ 2018 ዓ.ም ከቀነ- 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራች ጨረታውን አሸንፎ ባቀረበዉ ሰነድ መሰረት እቃዎቹን ሳያቀርብ ቢቀር ያስያዘው በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ድርጅቱ ገቢ ያደርጋል ወይም ተመላሽ አይሆንም።
- ጨረታ ሰነዶችና ከጨረታው ጋር ተያያዥ የሆኑ ሰነዶች ማለትም ቴክኒካል ዋናውና ኮፒ እና ፋይናንሻል ዋናውና ኮፒ ዶክመንት በፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያው ሰዓት በፊት ለዚህ በተዘጋጃው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ቁሳቁሶች በተቀመጠው ስፔሲፊኬሽን መሰረት መሆን አለበት።
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ተጫራጮቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ሳይቀይሩ በትእዛዙ መጠን እስከ 25 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው።
- ጨረታው ሀሙስ ታህሳስ 30/2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 8፡30 በጉርድ ሾላ በሚገኘው ሳሊህተ ምህረት ቤተክርስያን ፊት ፊት ለፊት ድራር ሞል አጠገብ በሚገኘዉ የማህበሩ መሰብሰቢያ አደራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- አሸናፊው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተገለፀለት ወይም የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ሞንታርቮውንና ሜጋፎን እስፒከር ከ7ቀን ባልበለጠ ጊዜ ወይም በውሉ መሰረት ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ቁሳቁሶች በድርጅቱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጫራቾች ስለጨረታዉ ተጨማሪ ማብራሪያ ሲፈልጉ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ስልክ በመደወል ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር፡ 011-515-06-08
