የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቁጥር 14/2018 በ2018 በጀት ዓመት በሚያካሂዳቸው ለሀገር ውስጥ ውድድሮች አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያየ መጠን ያላቸውን ደረጃውን የጠበቀ የሜዳሊያ፣ የዋንጫ እና ሪቫን ግዥ በሀገር ውስጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ ግልጽ
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቁጥር 14/2018 በ2018 በጀት ዓመት በሚያካሂዳቸው ለሀገር ውስጥ ውድድሮች አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያየ መጠን ያላቸውን ደረጃውን የጠበቀ የሜዳሊያ፣ የዋንጫ እና ሪቫን ግዥ በሀገር ውስጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፡-
- በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የታደስ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የቲን እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታውን በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ጉርድ ሾላ በሚገኘው በፌዴሬሽኑ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት 4፡30 ሰዓት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር5 (መሰብሰቢያ አዳራሽ) ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ለእያንዳንዱ ዕቃ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ እና ሳምፕል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የሚጫረቱት በዘርፉ የተሰማሩ መሆን አለባቸው።
አድራሻ፡- ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6
ለበለጠ መረጃ፡- 0116-47-97-94/ 0116-47-95-78 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ፋክስ - 0116-45-08-79 ፖ.ሳ.ቁ 13336
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
