Tender Detail

Tender Details


በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


የደቡብ ዕዝ የጨረታ ማስታወቂያ

የማስታወቂያ ቁጥር ደቡብ ዕዝ ግዥ A-2/2018

 

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

1.     አላቂ የፅህፈት ዕቃዎች እና የስልጠና መርጃ ዕቃዎች

2.     ዳት ዕቃዎች

3.     የስራ ቱታ

4.     የሽልማት ዕቃዎች

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች በጨረታው ሊወዳደር ይችላል፡፡

1.     ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው የጨረታ ዓይነቶች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የአቅራቢነት ምዝገባ የምስ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2.     የተጨማሪ እሴት ተመዝጋቢ /ከፋይነት/ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ

3.     የንግድ ምዝገባ ምስ ወረቀት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ

4.     የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ አለባቸው

5.     ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ለእያንዳንዱ ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መመሪያ መሠረት በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

6.     ተጫራቾች የሚመረቱበትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ የዕቃውን ዓይነት ኢንቨሎፑ ላይ በግልፅ መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡

7.     የጨረታ ሰነዱን ከተጫራቾች ዝርዝር መምሪያ ጋር የማይመለስ ብር 400.00 በመፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታውጆ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት ቀናት ውስጥ ቶጋ መከላከያ ሠራዊት ካምፕ በሚገኘው የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ግዥ ቢሮ መግዛት ይቻላል፡፡

8.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቶጋ መከላከያ ሠራዊት ካምፕ በሚገኘው /ዕዝ /መምሪያ ግዥ ቢሮ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል

9.     ጨረታው የካቲት 17 ቀን 2018 / ከረፋዱ 400 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ዕዝ መምሪያ ግዥ ቢሮ ጎን በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡

10. አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈፅሙ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል ያሸነፉበትን ዕቃ በራሳቸው ትራንስፖርት ወጭ በማጓጓዝ እና በማራገፍ ቶጋ መከላከያ ሠራዊት ካምፕ በሚገኘው የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ግምጃ ቤት ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ እንዲሁም 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ በስል ቁጥር 046-328-0020 ይደውሉ

 

የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ

ቶጋ

Save Tender