Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Athletics federation (የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን)
  • Address ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንጻ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116-47-97-94
  • Websitehttps://eaf.org.et/
  • Deadline06 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2026-01-06 00:00:00
  • Categories Audio Visual, Photography And Filming Service And Equipment

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቁጥር 16/2018 በተለያዩ ጊዜያት ለሚያካሂዳቸው ውድድሮች ለሚጠቀምበት የቪዲዮ እና ፎቶ ካሜራ ሌንስ ግዥ በተያዘው ስፔስፊኬሽን መሠረት በሀገር ውስጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቁጥር 16/2018 በተለያዩ ጊዜያት ለሚያካሂዳቸው ውድድሮች ለሚጠቀምበት የቪዲዮ እና ፎቶ ካሜራ ሌንስ ግዥ በተያዘው ስፔስፊኬሽን መሠረት በሀገር ውስጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

በዚሁ መሠረት፡-

  1. በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የቲን እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
  3. ተጫራቾች ጨረታውን በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ጉርድ ሾላ በሚገኘው በፌዴሬሽኑ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን ከቀኑ 800 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት 830 ሰዓት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 (መሰብሰቢያ አዳራሽ) ይከፈታል
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን እቃ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል
  7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
  8. ተጫራቾች የሚጫረቱት በዘርፉ የተሰማሩ መሆን አለባቸው

አድራሻ፡- ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንጻ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6

ለበለጠ መረጃ፡- 0116-47-97-94/ 01106-47-95-78 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

ፋክስ፡- 0116-45-08-79 .. 13336

 

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

 

Save Tender