በአብክመ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የስሪንቃ ግብርና ምርምር ማዕከል የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ለማዕከሉ አገልግሎት የሚውል በ2018 በጀት ዓመት ግዥ ለመፈፀም በሎት 1. ጎማ ሎት 2 የትራክተር መለዋወጫዎች እና የተለያዩ መፍቻዎች በግልፅ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በቁጥር 1
በአብክመ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የስሪንቃ ግብርና ምርምር ማዕከል የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ለማዕከሉ አገልግሎት የሚውል በ2018 በጀት ዓመት ግዥ ለመፈፀም በሎት 1. ጎማ ሎት 2 የትራክተር መለዋወጫዎች እና የተለያዩ መፍቻዎች በግልፅ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች ለማሳተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- በስራ ዘርፍ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፡፡
- የቫት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን፡፡
- ግዥው ከ20,000.00 /ሃያ ሺህ/ ብር በላይ ከሆነ ቫት ተቀንሶ ወደ መንግስት ገቢ የምናደርግ መሆኑን እንዲሁም 20,000,00 /ሃያ ሺህ/ ብር በላይ ከሆነ 3% ተቀንሶ ወደ መንግስት ገቢ የምናደርግ መሆኑን
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ ያላቸው
- ተጫራቾች መ/ቤቱ የጨረታቸውን ማንኛውን እቃ በኦርጅናል መሙላትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ያሸናፉባቸውን ማንኛውንም እቃ የራሳቸው ወጭ የማጓጓዣ የማስጫኛ እና ማስወረጃ እንድሁም ወደ እስቶር የማስገባት ወጭዎችን በመሸፈን ስሪንቃ ግብርና ምርምር ማዕከል ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ በሚነበብ መልኩ መፃፍና በየገፁ ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ተጫራቾች ማንኛንም ዋጋ ሲሞሉ ከእያንዳንዱ የእቃ ዋጋ ላይ ከነ ቫቱ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በትክክል ሞልተው በኦርጅናልና በኮፒ ሰነድ በ2 በተለያየ ፖስታ አሽገው ለዚው የተዘጋጀ ሳጥን በየሎቱ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በስሪንቃ ግብረና ምርምር ማዕከል ግዥ ፋይናስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ድረስ በመምጣት የማይመለስ 50.00 /አምሳ ብር ብቻ/ በመክፈል መወሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚህው ቀን ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች እና ሀጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሞሉትን ዋጋ 1% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በመ/ቤታችን ገቢ ደረሰኝ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ያሲያዙት Cpo በመሂ 1 የገቢ ደረሰኝ ከኦርጅናል ጨረታ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ማንኛውንም ማስረጃዎች ሆነ ጥሬ ገንዘብ በእጅ ይዞ መቅረብ አይችልም።
- ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው ከ5 የስራ ቀናት ብኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት መጥተው ውል መውሰድ እና በውሉ ላይ በተቀመጠው ቀን ገደብ በውሉ መሰረት መፈፀም አለበት፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማስረጃ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን የተሳሳተ ጨረታ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል በህግም ያስጠይቃል ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በካላደር ዝግ ከሆነ የሚቀጥለው ስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- በጨረታው አሸናፊ ከሆነ የውል ማስከበሪያ ዋስትና የውል ዋጋ 10% (Cpo) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም ኢንሹራንስ ማስያዝ ይኖርበታል ፣ውሉም ሊጠናቀቅ ተመላሽ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ 0333300090 /ሰሜን ወሎ ዞን ስሪንቃ /
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የስሪንቃ ግብርና ምርምር ማዕከል
