የአዳማ ከተማ አስተዳደር በከተማ አስተዳደሩ በመኖሪያ ቤቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ.ከ. አስተ.ገ.ጽ. ቤት 001/2018
የአዳማ ከተማ አስተዳደር በከተማ አስተዳደሩ በመኖሪያ ቤቶች ላይ የሚስተዋለውን የፍላጎትና የአቅርቦት አለመጣጣም ችግር ለመፍታት ወጪ ቆጣቢ ቤቶችን ገንብቶ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲችል በመንግስት በተመደበ ካፒታል በጀት በቦሌ ክፍለ ከተማ አንዶዴ ወረዳ በ4 ወራት ጊዜ ውስጥ ተገንብተው የተጠናቀቁ ባለ 5 ወለል 13 ብሎክ በቂ የመኪና ማቆሚያ ፡ የ24 ሰአት የውሃ እና መብራት አገልግሎት ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚሆን የጋራ ቦታ ፡ በቂ የልጆች መጫወቻ ቦታ እና የጋራ መናፈሻ ቦታ ያላቸው ባለ ሁለት መኝታ 390 የመኖሪያ ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ በ50% ቅድመ ክፍያ እና ቀሪው 50% ክፍያ እስከ ሰኔ 30/2018 ባለው ጊዜ ውስጥ ተከፍሎ በሚጠናቀቅ ስምምነት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ ይፈልጋል።
ስለሆነም ማንኛውም ለጨረታ የቀረቡ የመኖሪያ ቤቶችን ለመግዛት የሚፈልግ የአዳማ ከተማ ነዋሪ ፡ የምስራቅ ሸዋ ዞን አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች፡ የአዳማ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች፡ በአዳማ ከተማ የሚሰሩ የፌዴራል እና የክልል መንግስት መስሪያ ቤቶች ውሰጥ ተቀጥረው የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች እና በአዳማ ከተማ ውስጥ በተለያየ የግል ድርጅቶች ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ወይም ለሰራተኞቻቸው መግዛት የሚፈልጉ የመንግስት ወይም የግል ወይም የአክሲዮን ወይም ማህበራት ወይም ድርጅቶች ነዋሪነታቸው አዳማ ከተማ የሆነ ሁሉ የተጫራቹን ማንነት የሚገልጽ መታወቂያ (ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ) ለአክሲዮን ማህበራት ወይም ለድርጅቶች ከሚሰሩበት ክፍለ ከተማ ወይም ወረዳ የተጻፈ ደብዳቤ በመያዝ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ማታ 11፡30 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 ( አምስት መቶ ብር) በሲንቄ ባንክ የአካውንት ቁጥር 1054551161211 በመክፈል ከአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ደረሰኝ በመቁረጥ አዳማ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል። ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በተጫራቾች መመሪያ ላይ በተገለጸው ፕሮግራም መሰረት በከተማ አስተደዳሩ ህንፃ ቅጥር ግቢ ቦኩ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል። የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ላይ የሚውል ከሆነ በተከታዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል። መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የበለጠ መረጃ ከፈስጉ በ 09 38 70 91 02 ይደውሉ።
የአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
